መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 2:1-4

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 2:1-4 አማ2000

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤ ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፥ ንፍ​ታ​ሌም፥ ጋድ፥ አሴር። የይ​ሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፤ እነ​ዚህ ሦስቱ ከከ​ነ​ዓ​ና​ዊቱ ሴት ከሴዋ ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደ​ለ​ውም። ምራ​ቱም ትዕ​ማር ፋሬ​ስ​ንና ዛራን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ሁሉ አም​ስት ነበሩ።