መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 2
2
1የእስራኤልም ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤ 2ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር።
3የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴት ከሴዋ#በዘፍጥረት ምዕ. 38 ቍ. 2 እና 12 ላይ “ሴዋ ራስዋ እናት ናት” ልጅ ተወለዱለት። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደለውም። 4ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ።
5የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮም፥ ያሙሔል። 6የዛራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ኤማን፥ ካልኮል፥ ዳራ፤ ሁሉም አምስት ነበሩ። 7የዘምሪም ልጅ ከርሚ ነው፤ የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙን ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ። 8የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ።
9ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች፤ ኢያሬሄም፥ አራም፥ ካሌብ ነበሩ። 10አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳን ልጆች አለቃ ነአሶንን ወለደ፤ 11ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ 12ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ 13እሴይም የበኵር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሣማን፥ 14አራተኛውንም ናትናኤልን፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ 15ስድስተኛውንም አሶንን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ወለደ፤ 16እኅቶቻቸውም ሶርህያና አቢግያ ነበሩ። የሶርህያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ። 17አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ይትኤር ነበረ።
18የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ዐዙባ የምትባል ሚስት አገባ፥ ይሪዖትንም አገባ፤ ልጆችዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ ኤርኖን ነበሩ። 19ዐዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርስዋም ኦርን ወለደችለት። 20ኦርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
21ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ ስድሳ አምስት ዓመት” ይላል። በሆነው ጊዜ ወደ አገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉብንም ወለደችለት። 22ሴጉብም ኢያኤርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት። 23ኤስሮምም ጌሱርንና አራምን የኢያዔርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰደ። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ከተሞች ነበሩ። 24ኤስሮምም ከሞተ በኋላ ካሌብ ወደ ኤፍራታ መጣ። የኤስሮምም ሚስት አብያ የቴቁሔን አባት አስሖርን ወለደችለት።
25የኤስሮምም የበኵር ልጁ የኢያሬምሄል ልጆች በኵሩ ራም፥ በአናን፥ አራን፥ አሶም፥ አኪያ#“አኪያ” የሚለው በብዙ የግሪክኛና የዕብ. ዘርዕ “ወንድሙ” ይላል። ነበሩ። 26ለኢያሬምሄልም አጥራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርስዋም የአናም እናት ነበረች። 27የኢያሬምሄል የበኵሩ የራም ልጆች ማኦስ፥ ኢያቢን ዔቄር ነበሩ። 28የአናምም ልጆች ሸማይና ያዳይ ነበሩ። የሸማይም ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ። 29የአቢሱርም ሚስት ስም አቢካኤል ነበረ፤ እርስዋም፥ አዛቡርንና ሞሊድን ወለደችለት። 30የናዳብም ልጆች ሴሌድና አፋይም ነበሩ፤ ሴሌድም ልጆችን ሳይወልድ ሞተ። 31የአፋይምም ልጅ ይሲ፥ የይሲም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ። የአሕላይም ልጅ ይዳይ ነበረ። 32የይዳይ ልጆች አክሲም፥ ዮቴርና ዮናታን ነበሩ፤ ዮቴርም ልጆችን ሳይወልድ ሞተ። 33የዮናታንም ልጆች ፋሌትና አዛዝ ነበሩ፤ እነዚህም የኢያሬምሔል ልጆች ነበሩ። 34ለሶሳንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ለሶሳንም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው። 35ሶሳንም ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ልጁን አጋባት፥ እርስዋም ያቲን ወለደችለት። 36ያቲም ናታንን ወለደ፤ ናታንም ዛቤትን ወለደ፤ 37ዛቤትም አውፋልን ወለደ፤ አውፋልም ዖቤድን ወለደ፤ 38ዖቤድም ኢያሁን ወለደ፤ ኢያሁም አዛርያስን ወለደ፤ 39አዛርያስም ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስም ኤልዓሳን ወለደ፤ 40ኤልዓሳም ሲስማኤልን ወለደ፤ ሲስማኤልም ሱላምን ወለደ፤ 41ሱላምም ኢዮቆምን ወለደ፤ ኢዮቆምም ኤልሳማን ወለደ።
42የኢያሬምሄል ወንድም የካሌብ ልጆች በኵር የዚፍ አባት ማሪስ ነው፤ የኬብሮንም አባት የማሪስ ልጆች ነበሩ። 43የኬብሮንም ልጆች፤ ቆሬ፥ ተፋ፥ ሬቆምና፥ ሴማዓ ነበሩ። 44ሴማዓም የኤርቃምን አባት ራኤምን ወለደ፤ ኤርቃምም ሰማኤምን ወለደ። 45የሰማኤምም ልጅ ማዖን ነበረ፤ ማዖንም የቤት ሱር አባት ነበረ። 46የካሌብም ዕቅብት ጌፋ አራንን፥ ሞሳን፥ ጋዜዝን ወለደች። አራንም ጊዚኢን ወለደ። 47የያዳይም ልጆች፤ ሬጌም፥ ዮታም፥ ጌርሶም፥ ፋሌጥ፥ ጌፋና፥ ሰጋፍ ነበሩ። 48የካሌብም ዕቅብት ማዕካ ሴብርንና ቲርሐናን ወለደች። 49ደግሞም የምድሜናን አባት ስጋብን የመክቢናንና የጌባልን አባት ሳዑልን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ አስካ ነበረች።
50የካሌብም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የኤፍራታ የበኵሩ የኦር ልጅ የቀርያታርም አባት ሶባል ነበር፥ 51የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት ጋዲር አባት ኦሪ። 52የቀርያታርምም አባት የሶባል ልጆች አረኤ፥ ሃጼ፥ አማኒት ነበሩ። 53የቀርያታርም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፋታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሸራውያን፤ ከእነዚህም ሶራሐውያንና ኤሽታአላውያን ወጡ። 54የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥ አጦሮት ቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ሰራዓውያንም ነበሩ። 55በያቤጽም የተቀመጡ የጸሓፊዎች ወገኖች፤ ቴርዓውያን፥ ሹማታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ