የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 1

1
ከአ​ዳም እስከ አብ​ር​ሃም ያለው ሐረገ ትው​ልድ
(ዘፍ. 5፥1-3210፥1-3211፥10-26)
1አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥ 2ቃይ​ናን፥ መላ​ል​ኤል፥ ያሬድ፥ 3ሄኖክ፥ ማቱ​ሳላ፥ ላሜሕ፥ 4ኖኅ፥ ልጆ​ቹም#“ልጆ​ችም” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ሴም፥ ካም፥ ያፌት።
5የያ​ፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ይሕ​ያን፥ ኤልሳ፥#“ኤልሳ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ቶቤል፥ ሞሳ​ሕና ቲራም። 6የጋ​ሜ​ርም ልጆች አስ​ካ​ናስ፥ ሪፋት፥ ቶር​ጋማ። 7የይ​ሕያ ልጆች ኤልሳ፥ ተር​ሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ።
8የካ​ምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን። 9የኩ​ሽም ልጆች፤ ሳባ፥ ኤው​ላጥ፥ ሳበታ፥ ሬግ​ማን፥ ሱቦን። የሬ​ግ​ማ​ንም ልጆች፤ ሴባ፥ ዳዳን። 10ኩሽም ናም​ሩ​ድን ወለደ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ አዳ​ኝና#“አዳኝ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ኀያል መሆ​ንን ጀመረ። 11ምሥ​ራ​ይም ሎዲ​አ​ምን፥ ዐና​ኒ​ምን፥ ሎቢ​ንን፥ ንፍ​ታ​ሌ​ምን፥ 12ጴጥ​ሮ​ሳ​ኒ​ኤ​ምን፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የወ​ጡ​በ​ትን ከሰ​ሎ​ን​ኤ​ምን፥ ከፋ​ቱ​ሪ​ምን ወለደ። 13ከነ​ዓን የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥ 14ኤያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥ 15አዌ​ዎ​ንን፥ አረ​ቄ​ዎ​ንን፥ ኤሴ​ነ​ዎ​ንን፥ 16አራ​ዴ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ሬ​ዎ​ንን፥ አማ​ቲን ወለደ።
17የሴ​ምም ልጆች፤ አይ​ላም፥ አሡር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ የአ​ራ​ምም ልጆች፤ ኡስ፥ ዑል፥ ጋቴር፥ ሞሳክ። 18አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን#ዕብ. “ቃይ​ና​ንን” አይ​ጽ​ፍም። ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦ​ርን ወለደ። 19ለኤ​ቦ​ርም ሁለት ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በዘ​መኑ ምድር ተከ​ፋ​ፍ​ላ​ለ​ችና የአ​ን​ደ​ኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ዮቅ​ጣን ነበረ፤ 20ዮቅ​ጣ​ንም ኤል​ሞ​ዳ​ድን፥ ሣሌ​ፍን፥ ኤራ​ሞ​ትን፥ ያራ​ሕን፥ 21ቄዱ​ራ​ምን፥ ኤዜ​ልን፥ ዲቅ​ላ​ምን፥ 22ጌማ​ሄ​ልን፥ ኤል​ሜ​ሄ​ልን፥ ሳባን፥ 23ኦፌ​ርን፥ ሄው​ላን፥ ኦራ​ምን፥ ዑካ​ብን#“ዑካ​ብን” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ነበሩ። 24የሴ​ምም ልጆች፤ አይ​ላም፥ አሡር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሳላን፥ ቃይ​ናን፥#ዕብ. “ቃይ​ና​ንን” አይ​ጽ​ፍም። 25ዔቦር፥ ፋሌቅ፥ ራግው፥ 26ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥ 27አብ​ር​ሃም የተ​ባ​ለው አብ​ራም።
የይ​ስ​ማ​ኤል ሐረገ ትው​ልድ
(ዘፍ. 25፥12-16)
28የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ልጆች፤ ይስ​ሐቅ፥ ይስ​ማ​ኤል። 29ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም እን​ደ​ዚህ ነው። የይ​ስ​ማ​ኤል በኵር ልጅ ናቢ​ዎት፤ ቄዳር፥ ቢዲ​ሄል፥ ሙባ​ሳን፥ 30ሚስ​ማዕ፥ ይዱማ፥ ማሴ፥ ኬዲድ፥ ቴማን፤ 31የጡር፥ ናፌስ፥ ቂዳማ፤ እነ​ዚህ የይ​ስ​ማ​ኤል ልጆች ናቸው።
32የአ​ብ​ር​ሃም ዕቅ​ብት ኬጡራ የወ​ለ​ደ​ች​ለት ልጆች፤ ዘም​ራን፥ ዮቅ​ሳን፥ ሜዳም፥ ምድ​ያን፥ ዮሳ​ብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮ​ቅ​ሳ​ንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን። 33የም​ድ​ያ​ምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖሕ፥ አቢ​ዳን፥ ኤል​ዳን። እነ​ዚህ ሁሉ የኬ​ጡራ ልጆች ነበሩ።
የኤ​ሳው ሐረገ ትው​ልድ
(ዘፍ. 36፥1-9)
34አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ወለደ። የይ​ስ​ሐ​ቅም ልጆች ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ነበሩ። 35የዔ​ሳው ልጆች፤ ዔል​ፋዝ፥ ራጉ​ኤል፥ ይዑል፥ ይጉ​ሎም፥ ቆሬ። 36የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ሳፍር፥ ጎታም፥ ቄኔዝ፥ ቴም​ናስ፥ አማ​ሌቅ። 37የራ​ጉ​ኤል ልጆች፤ ናቦት፥ ዛራ፥ ሴዴት፥ ሞዛ።
38የሴ​ይ​ርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሳባን፥ ሴቤ​ጎን፥ ዓናን፥ ዴሶን፥ አሦር፥ ዴሳን። 39የሎ​ጣ​ንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ኤማን፤ ታም​ናን የሎ​ጣን እኅት ነበ​ረች። 40የሦ​ባል ልጆች፤ ጎለም፥ ማኔ​ሐት፥ ኔባል፥ ሳፍር፥ አናን፤ የሴ​ቤ​ጎን ልጆች፤ ሐያን፥ አናም፤ 41የአ​ናም ልጆች፤ ዴሶን፥ የአ​ናም ሴት ልጅ ኤሌማ፥ የዴ​ሶ​ንም ልጆች፤ አም​ዳን፥ ኤስ​ቦን፥ ኢይ​ት​ራን፥ ካራን፥ እሊህ ናቸው። 42የአ​ሦር ልጆች፤ በለ​ዓን፥ ዛዕ​ዋን፥ ኢይ​ዓ​ቃን። የዴ​ሶን ልጆች፤ ዖስ፥ አራን።
የኤ​ዶም ነገ​ሥ​ታት
(ዘፍ. 36፥32-43)
43በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይ​ነ​ግሥ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር የነ​ገሡ ነገ​ሥ​ታት እነ​ዚህ ናቸው። የቢ​ዖር ልጅ ባላቅ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ዲናባ ነበረ። 44ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የባ​ሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ። 45ኢዮ​ባ​ብም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የቴ​ማን ሀገር ሰው አሶም ነገሠ፤ 46አሶ​ምም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ በሞ​ዓብ ሜዳ ምድ​ያ​ምን የመ​ታው የባ​ራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ጌቴም ነበረ። 47አዳ​ድም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የማ​ስቃ ሰው ስማዓ ነገሠ። 48ስማ​ዓም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ በወ​ንዙ አጠ​ገብ ያለ​ችው የረ​ኆ​ቦት ሰው ሳኦል ነገሠ። 49ሳኦ​ልም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የአ​ክ​ቦር ልጅ በኣ​ል​ሐ​ናን ነገሠ። 50የአ​ክ​ቦር ልጅ በኣ​ል​ሐ​ና​ንም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የባ​ራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ፌጎር ነበረ፤ ሚስ​ቱም የሚ​ዛ​ሃብ ልጅ የመ​ጥ​ሬድ ልጅ መሄ​ጣ​ብ​ኤል ነበ​ረች።
51አዳ​ድም ሞተ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም አለ​ቆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቴም​ናዕ አለቃ፥ ጎለም አለቃ፥ የቴት አለቃ፥ 52አህ​ሊ​ባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፌኖን አለቃ፥ 53ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ መብ​ሳር አለቃ፥ 54መግ​ዴ​ኤል አለቃ፥ ዛፎ​አል አለቃ፤ እነ​ዚህ የኤ​ዶ​ም​ያስ አለ​ቆች ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ