የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 11

11
ዳዊት በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገሠ
(2ሳሙ. 5፥1-10)
1እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በኬ​ብ​ሮን ወደ ዳዊት ተሰ​ብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን፤ 2አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን አንተ ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ” አለህ። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ረገ፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም እጅ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት።
4ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ኢያ​ቡስ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ በሀ​ገ​ሩም የተ​ቀ​መጡ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን በዚያ ነበሩ። 5በኢ​ያ​ቡ​ስም የተ​ቀ​መጡ ዳዊ​ትን፥ “ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም” አሉት፤ ዳዊት ግን አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት። 6ዳዊ​ትም ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያ​ንን አስ​ቀ​ድሞ የሚ​መታ ሰው አለ​ቃና መኰ​ንን ይሆ​ናል አለ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ ኢዮ​አብ አስ​ቀ​ድሞ ወጣና ወጋ​ቸው፥ አለ​ቃም ሆነ። 7ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ስለ​ዚ​ህም “የዳ​ዊት ከተማ” ብለው ጠሩ​አት። 8ዳዊ​ትም የከ​ተ​ማ​ዋን ዙሪያ ቀጸረ፤ ተዋ​ግ​ቶም እጅ አደ​ረ​ጋት።#ዕብ. “ኢዮ​አ​ብም ከሚ​ሎን ጀምሮ የቀ​ረ​ውን ከተማ አበጀ” የሚል ይጨ​ም​ራል። 9ዳዊ​ትም ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና እየ​በ​ረታ ሄደ።
የዳ​ዊት ኀያ​ላን
(2ሳሙ. 23፥8-39)
10ለዳ​ዊ​ትም የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስለ እስ​ራ​ኤል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር በመ​ን​ግ​ሥቱ አጸ​ኑት። 11የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን ቍጥር ይህ ነበረ፤ የሠ​ላ​ሳው አለቃ የአ​ኪ​ማን ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ ነበረ፤ እርሱ ጦሩን አን​ሥቶ ሦስት መቶ ሰው በአ​ንድ ጊዜ ገደለ። 12ከእ​ር​ሱም በኋላ በሦ​ስቱ ኀያ​ላን መካ​ከል የነ​በረ የአ​ሆ​ሃ​ዊው የዱዲ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ። 13እርሱ ከዳ​ዊት ጋር በፋ​ሶ​ደ​ሚን ነበረ፥ በዚ​ያም ገብስ በሞ​ላ​በት እርሻ ውስጥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለሰ​ልፍ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ። 14በእ​ር​ሻ​ውም መካ​ከል ቆመው ጠበ​ቁት፥ ያች​ንም ቦታ አዳ​ናት፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ማዳን አዳ​ና​ቸው።
15ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ዳዊት ወዳ​ለ​በት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ሰፍሮ ነበር። 16በዚ​ያም ጊዜ ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በቤተ ልሔም ነበረ። 17ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ይሰ​ጠ​ኛል?” ብሎ ተመኘ። 18እነ​ዚህ ሦስቱ ኀያ​ላን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሰፈር ሰን​ጥ​ቀው ሄዱ፥ በበ​ሩም አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘ​ውም ለዳ​ዊት አመ​ጡ​ለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አል​ወ​ደ​ደም፥ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ​ስሶ፦ 19“ይህን አደ​ርግ ዘንድ አም​ላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለሞት አሳ​ል​ፈው አም​ጥ​ተ​ው​ታ​ልና የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ደም እጠ​ጣ​ለ​ሁን?” አለ። ስለ​ዚ​ህም ዳዊት ይጠ​ጣው ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስ​ቱም ኀያ​ላን ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።
20የኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይ​ፉ​ንም በሦ​ስት መቶ ላይ አን​ሥቶ በአ​ንድ ጊዜ ገደ​ላ​ቸው፤ በሦ​ስ​ቱም መካ​ከል ስሙ የተ​ጠራ ነበረ። 21በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሆ​ኑት በሦ​ስቱ መካ​ከል የከ​በረ ነበረ፥ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።
22በቀ​በ​ሳ​ኤል የነ​በ​ረው፥ ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የጽ​ኑዕ ሰው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ እንደ አን​በሳ ኀያ​ላን የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት የሞ​ዓብ ሰዎች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ይም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ። 23ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ረጅ​ሙን ግብ​ፃ​ዊ​ውን ሰው ገደለ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ የሸ​ማኔ መጠ​ቅ​ለያ የመ​ሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው። 24የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ያደ​ረ​ገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ኀያ​ላን መካ​ከል የተ​ጠራ ነበረ። 25እነሆ፥ ከሠ​ላ​ሳው ይልቅ የከ​በረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም። ዳዊ​ትም በና​ያ​ስን በሀ​ገሩ#ዕብ. “በዘ​በ​ኞቹ” ይላል። ላይ ሾመው።
26ደግ​ሞም በጭ​ፍ​ሮቹ ዘንድ የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን እነ​ዚህ ናቸው፤ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አሣ​ሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤል​ያ​ናን፤ 27ሃሮ​ራ​ዊው ሳሞት፥ ፈሎ​ና​ዊው ኬሌስ፤ 28የቴ​ቁሔ ሰው የአ​ቂስ ልጅ ኦራ፥ ዓና​ቶ​ታ​ዊው አቤ​ዔ​ዜር፤ 29ኩሳ​ታ​ዊው ሰቦ​ካይ፥ የአ​ሆ​ሂው ዔላይ፤ 30ነጦ​ፋ​ዊው ሜሐሪ፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊው የበ​ዓና ልጅ ሔሌድ፤ 31ከብ​ን​ያም ወገን ከጊ​ብዓ የሪ​ባይ ልጅ ኢታይ፥ ፈር​ኖ​ታ​ዊው ባን​ያስ፤ 32የገ​ዓዝ ወንዝ ሰው ኡሪ፥ ገራ​ባ​ታ​ዊው አብ​ኤል፥ 33ባሮ​ማ​ዊው ዓዝ​ሞት፥ ሰዓ​ል​ቦ​ና​ዊው ኤሊ​ያ​ሕባ፤ 34የጊ​ዞ​ን​ያ​ዊው የኤ​ሳም ልጅ፥ የአ​ሩ​ራ​ዊው የሶላ ልጅ ዮና​ታን፤#ምዕ. 11 ቍ. 34 ግእ​ዙና ግሪክ ሰባ. ሊ. ቢመ​ሳ​ሰ​ሉም በዕብ. የስም ልዩ​ነት ይታ​ያል። 35የአ​ሮ​ራ​ዊው የሳ​ኮር ልጅ አህ​ያም፥ የኤር ልጅ ኤሊ​ፋል፤ 36መከ​ራ​ታ​ዊው ኦፌር፥ ፍሎ​ና​ዊው አኪያ፤ 37ቀር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው ሴራይ፥#ዕብ. “ሐጽሮ” ይላል። የኤ​ዝ​ባይ ልጅ ናራይ፤ 38የና​ታ​ንም ወን​ድም ኢዩ​ኤል፥ የሐ​ገሪ ልጅ ሚብ​ሐር፤ 39አሞ​ና​ዊው ሴሌቅ፥ የሦ​ር​ህያ ልጅ የኢ​ዮ​አብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ​ታ​ዊው ናኮር፤ 40ይት​ራ​ዊው ዔራ፥ ይት​ራ​ዊው ጋሬብ፤ 41ኬጢ​ያ​ዊው ዑር​ያስ፥ የአ​ሕ​ላይ ልጅ ዘባት፤ 42የሮ​ቤ​ላ​ዊው የሲዛ ልጅ ዓዲና፥ እርሱ የሮ​ቤ​ላ​ው​ያን አለቃ ነበረ ከእ​ር​ሱም ጋር ሠላሳ ሰዎች ነበሩ፤ 43የሞካ ልጅ ሐናን፥ ሚት​ና​ዊው ኢዮ​ሣ​ፍጥ፤ 44አስ​ታ​ሮ​ታ​ዊው ዖዝያ፥ የአ​ሮ​ዔ​ራ​ዊው የኮ​ታም ልጆች ሳማና ይዒ​ኤል፤ 45የሳ​ምሪ ልጅ ይዳ​ኤል፥ ወን​ድ​ሙም ቲዳ​ዊው ዮዛሔ፥ 46መዓ​ዊው ኤሊ​ኤል፤ ኢያ​ር​ባኢ፥ ልጁ ዮሳኢ፥ ኤል​ነ​ዓ​ምና ሞዓ​ባ​ዊው ይትማ፤ 47ኤሊ​ኤል፥ ዖቤድ፥ ምሶ​ባ​ዊው ኢያ​ስ​ኤል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ