ትንቢተ ሶፎንያስ መግቢያ
መግቢያ
ነቢዩ ሶፎንያስ መልእክቱን ያስተላለፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባተኛው ምእተ ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ነው፤ ምናልባትም ትንቢቱ የተተነበየው ንጉሥ ኢዮስያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በስድስት መቶ ኻያ አንድ ዓመት የቃል ኪዳን ተሐድሶ ከማድረጉ ዐሥር ዓመት ቀደም ብሎ ሊሆን ይችላል። መጽሐፉ ሌሎች ነቢያት የተናገሩትን ትንቢት የያዘ ነው፤ እነርሱም ይሁዳ ለባዕዳን አማልክት በመስገዷ ምክንያት ስትቀጣ ጥፋትና መደምሰስ እንደሚደርስባት የሚያመለክቱ ናቸው፤ እንዲሁም እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ሌሎችንም ሕዝቦች እንደሚቀጣ ይገልጣል። በኢየሩሳሌም ላይ የመፍረስ አደጋ ቢደርስባትም ከጊዜ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ሁኔታዋ ትመለሳለች፤ ትሑታንና ጻድቃንም ይኖሩባታል።
የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት
1. በይሁዳ ላይ የሚተላለፍ ፍርድ (1፥1-18)
2. ንስሓ መግባት (2፥1-3)
3. በእስራኤል ጐረቤቶች የሚተላለፍ ፍርድ (2፥4-15)
4. ይሁዳና ሌሎች ወገኖች ወደ ጌታ መመለሳቸው (3፥1-20)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ትንቢተ ሶፎንያስ መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ