ትንቢተ ዕንባቆም 3
3
የነቢዩ ጸሎት
1የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በሺግዮኖት።
2ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥
በዓመታት መካከል አድሰው፥
በዓመታት መካከል አስታውቀው፥
በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።
3እግዚአብሔር ከቴማን፥
ቅዱሱም ከፓራን ተራራ መጣ።
(ሴላ) ውበቱ ሰማያትን ሸፍኖአል፥
ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።
4ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥
ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤
ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።
5ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥
መቅሠፍትም ከእግሩ ይወጣል።
6ቆመ፥ ምድርንም አንቀጠቀጣት፥
ተመለከተ፥ ሕዝቦችንም አስደነገጠ፥
የዘለዓለም ተራሮች ተናጉ፥
የጥንት ኮረብቶች አጎነበሱ፥
የጥንት መንገዶች የእርሱ ናቸው።
7የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥
የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።
8ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን?
ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን?
በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።
9ቀስትህን ገለጥህ በቃልህ እንደ ማልህ
መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤
ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።
10ተራሮች አንተን አይተው ተወራጩ፥
የውኃ ወጀብ አለፈ፥
ጥልቁም ድምፁን ሰጠ፥
እጁንም ወደ ላይ አነሳ።
11በቀስቶችህ ብርሃን፥
በጦርህ መብረቅ ፀዳል፥
ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቀጥ ብለው ቆሙ።
12በቁጣ ምድርን ረገጥሃት፥
አሕዛብን በንዴት አሄድሃቸው።
13ሕዝብህን ለመታደግ፥
የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤
የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፥
ከመሠረቱ እስከ አንገቱ ድረስ አራቆትህ።
14ደስታቸው የተደበቁ ችግረኞችን እንደሚውጥ የሆነውን፥
እኛን ሊበትኑ እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጡትን፤
የጦረኛውን ራስ በገዛ ጦሩ ወጋህ፤
15በፈረሶችህ በባሕር ላይ ተራመድህ፥
ብዙ ውኆችንም ረገጥህ።
16እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥
ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤
መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥
በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥
በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥
የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።
17የበለስ ዛፍ ባታብብም፥
በወይን ተክሎች ላይ ፍሬ ባይገኝ፥
የወይራ ምርት ቢቋረጥ፥
እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥
በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥
ከብቶችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
18እኔ ግን በጌታ ደስ ይለኛል፤
በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
19 #
2ሳሙ. 22፥34፤ መዝ. 18፥33። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤
እግሮቼን እንደ ዋላ#3፥19 ዕብራይስጡ “እንደ ዋላ እግሮች” ሳይሆን “እንደ ዋላ” ብቻ ይላል። እግሮች ያደርጋል፤
በከፍታዎቼም ላይ ያስሄደኛል።
ለመዘምራን አለቃ፥
በባለ አውታር መሣሪያዎቼ።
Currently Selected:
ትንቢተ ዕንባቆም 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ