የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 2

2
ሁለተኛ ራእይ፦ አራቱ ቀንዶችና አራቱ አንጥረኞች
1ዐይኖቼንም አንሥቼ እነሆም አራት ቀንዶች አየሁ። 2#ዘዳ. 33፥17፤ ዳን. 7፥8።ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፦ “እነዚህ ይሁዳን፥ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ ቀንዶች ናቸው” ብሎ መለሰልኝ።
3ጌታም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ። 4#ኤር. 48፥25።እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልኩት። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሯቸው፥ የይሁዳንም አገር ለመበተን ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊቆርጡ መጥተዋል” ብሎ ተናገረ።
ሦስተኛ ራእይ፦ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰው
5 # ኤር. 31፥38-39፤ ሕዝ. 41፥13፤ ራእ. 11፥1፤ 21፥15። ዐይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ። 6እኔም፦ “አንተ ወዴት ነው የምትሄደው?” አልኩት። እርሱም፦ “ኢየሩሳሌምን ልለካትና ወርድና ርዝመቷ ስንት መሆኑን ለማየት ነው የምሄደው” አለኝ።
7እነሆም፥ ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ሌላ መልአክ ሊገናኘው እንደመጣ እርሱም ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ 8#ኢሳ. 49፥19-20፤ 54፥2-3፤ ኤር. 31፥27፤ ሕዝ. 38፥11።“ሩጥ፥ ይህንም ጎልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ትሆናለች። 9#ራእ. 21፥23፤ 22፥3-5።እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በመካከሏም ክብር እሆናለሁ፥ ይላል ጌታ።”
የመጀመሪያዎቹ ሦስት ራእዮች ጭብጦች
10 # ዘካ. 6፥5፤ ኢሳ. 48፥20፤ ኤር. 50፥8፤ 51፥6። ተነሡ! ተነሡ! ከሰሜን ምድር ሽሹ፥ ይላል ጌታ፤ እንደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፥ ይላል ጌታ። 11አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ፥ ተነሽ፥ ኰብልይ። 12#ዘዳ. 32፥10፤ መዝ. 17፥8።የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ ዘረፏችሁ አሕዛብ ልኮኛል፥ የሚነካችሁ በቀጥታ እኔን የዓይኔን ብሌን ይነካል። 13#ኢሳ. 14፥2፤ ሶፎ. 3፥15።እነሆ፥ እጄን በላያቸው ላይ አነሣለሁ፥ በምርኮ ተገዝተውላቸው ለነበሩት ራሳቸው በምርኮ ይዘረፋሉ፤ የሠራዊት ጌታም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
14የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ መጥቼ በመካከልሽ ስለምኖር ዘምሪ ደስም ይበልሽ! ይላል ጌታ። 15#ኢሳ. 56፥6፤ 66፥18።በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ ጌታ ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፥ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ። 16#ዘካ. 1፥17።ጌታም ይሁዳን እድል ፈንታው አድርጎ በተቀደሰችው ምድር ይወርሰዋል፥ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣታል። 17#ዕን. 2፥20፤ ሶፎ. 1፥7፤ ራእ. 8፥1።ጌታ ከተቀደሰ ማደሪያው ነቅቶአልና፥ ሰው ሁሉ፥ በፊቱ ዝም ይበል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ