ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሊያጸና፤ ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ ለተገረዙት አገልጋይ ሆነ እላለሁ፤ አሕዛብ ስለ ምሕረቱ እግዚአብሔርን እንዲያከብሩት፥ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ፤” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። እንደገናም “አሕዛብ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤” ይላል። እንደገናም “አሕዛብ ሁላችሁ! ጌታን አመስግኑ፤ ሕዝቦቹም ሁሉ ያመስግኑት፤” ደግሞም ኢሳይያስ “የእሴይ ሥር አሕዛብንም ሊገዛ የሚነሣው ይሆናል፤ በእርሱ አሕዛብ ተስፋ ያደርጋሉ፤” ይላል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 15 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ሮሜ ሰዎች 15
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮሜ ሰዎች 15:8-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos