ወደ ሮሜ ሰዎች 15:15-17

ወደ ሮሜ ሰዎች 15:15-17 መቅካእኤ

ነገር ግን አንዳንድ ነገሮችን ላስታውሳችሁ ፈልጌ ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ መሰረት በድፍረት ጻፍሁላችሁ። በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው። እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሆነ ነገር የምመካበት አለኝ።