ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔርን ፈተኑት፥ ዐመፁበትም፥ ትእዛዙንም አልጠበቁም፥ ተመለሱም እንደ አባቶቻቸውም ከዱ፥ እንደ ጠማማ ቀስትም ተገለበጡ፥ በኰረብታ መስገጃዎቻቸውም አስቈጡት፥ በተቀረጹ ምስሎቻቸውም አስቀኑት። እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፥ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ፥ የሴሎምን ማደሪያ ተዋት በሰዎች መካከል ያደረባትን ድንኳኑን፥ ኃይላቸውን ለምርኮ፥ ሽልማቱንም በጠላት እጅ ሰጠ። ሕዝቡንም በጦር ውስጥ ዘጋቸው፥ በርስቱም ላይ ንዴቱን ገለጠ። ጉልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፥ ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አላዩም። ካህኖቻቸውም በሰይፍ ወደቁ፥ መበለቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም። ጌታ ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ በወይን ኃይል እንደተበረታታ ጀግና፥ ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፥ የዘለዓለምን ውርደት አከናነባቸው። የዮሴፍንም ድንኳን ተዋት፥ የኤፍሬምንም ወገን አልመረጠውም፥ የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ። መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፥ ለዘለዓለምም በምድር ውስጥ መሠረታት። ዳዊትንም ባርያውን መረጠው፥ ከበጎቹም መንጋ ውስጥ ወሰደው፥ ከሚያጠቡ በጎችም በኋላ፥ ባርያውን ያዕቆብን ርስቱንም እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ ወሰደው። በልቡ ቅንነት ጠበቃቸው፥ በእጁም ብልሃት መራቸው።
መዝሙረ ዳዊት 78 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 78:56-72
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos