የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 7

7
1ስለ ብንያማዊ ሰው ስለ ኩዝ ቃል ለጌታ የዘመረው የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 6፥5፤ 22፥21። አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥
ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥
3ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሩዋት፥
የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
4አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥
ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥
5መልካም ላደረጉልኝም ክፉን መልሼላቸው ከሆነ፥
ጠላቴንም በከንቱ ገፍቼው ከሆነ፥
6 # መዝ. 143፥3። ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥
ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥
ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።
7 # መዝ. 9፥4፤ 19፥15። አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፥
በጠላቶቼ ላይ በቁጣ ተነሣባቸው፥
አቤቱ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ።
8የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፥
በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ።
9ጌታ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፥
አቤቱ፥ እንደጽድቄ ፍረድልኝ፥
እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።
10 # መዝ. 17፥3፤ 26፥2፤ 35፥24፤ 43፥1፤ 139፥23፤ ኤር. 17፥10፤ 20፥12፤ ራእ. 2፥23። የክፉዎች በደል ይጥፋ፥
ጻድቁን ግን አቅና፥
እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራል።
11 # መዝ. 3፥4። ጋሻዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው
ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው።
12እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፥
ሁልጊዜ ትክክለኛ ፈራጅ ነው፥
13 # መዝ. 11፥2። ለማይመለስ#7፥13 ንስሐ ለማይገባ ግን ሰይፉን ይስላል፥
ቀስቱን ወጥሮአል አዘጋጅቷልም፥
14 # ኢሳ. 50፥11። የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥
ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።
15 # ኢዮብ 15፥35፤ ኢሳ. 59፥4። እነሆ፥ ክፋትን ያማጠ
ተንኮልን ፀነሰ፥ ውሸትንም ወለደ።
16 # መዝ. 9፥16፤ 35፥8፤ 57፥7፤ ምሳ. 26፥27፤ መክ. 10፥8፤ ሲራ. 27፥26። ጉድጓድን ማሰ ቈፈረም።
በሠራውም ጉድጓድ ይወድቃል።
17ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥
ዓመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።
18 # መዝ. 18፥50፤ 30፥5፤ 135፥3፤ 146፥2። ጌታን ስለ ጽድቁ አመሰግነዋለሁ፥
ለልዑል ጌታም ስም እዘምራለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ