መዝሙረ ዳዊት 61
61
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
2አምላክ ሆይ፥ ጩኸቴን ስማ፥
ጸሎቴንም አድምጥ።
3ልቤ ተስፋ በቈረጠ ጊዜ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥
ከፍ ባለ ዓለት ላይ ትመራኛለህ።
4 #
መዝ. 46፥2። በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ፥
መጠጊያዬም ሆነኸኛልና።
5 #
መዝ. 17፥8፤ 36፥8፤ 57፥2። በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፥
በክንፎችህም ጥላ እጋረዳለሁ፥
6አቤቱ፥ አንተ ስእለቴን ሰምተሃልና፥
ስምህንም ለሚፈሩ ርስትን ሰጠሃቸው።
7 #
መዝ. 21፥5። ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ፥
ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ።
8 #
መዝ. 72፥5፤ 89፥5፤30፤37፤ 85፥11፤ 89፥15፤25፤ ምሳ. 20፥28። በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፥
ይጠብቁት ዘንድ ቸርነትንና እውነትን አዘጋጅለት።
9እንዲሁ ለስምህ ለዘለዓለም እዘምራለሁ
ስእለቴን ሁልጊዜ እፈጽም ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 61: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ