መዝሙረ ዳዊት 49
49
1ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፥
በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፥
3ዝቅተኞችና ከፍተኞች፥
ሀብታሞችና ድሆች በአንድነት።
4 #
መዝ. 78፥2፤ ማቴ. 13፥35። አፌ ጥበብን ይናገራል፥
የልቤም አስተንትኖ ማስተዋልን።
5ጆሮዬን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፥
በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።
6በደል ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ
በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
7 #
ኢዮብ 31፥24። በኃይላቸው የሚታመኑ፥
በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥
8 #
ምሳ. 10፥15፤ 11፥4፤ ሕዝ. 7፥19፤ ማቴ. 16፥26። በእውነት ማንም እራሱን አያድንም፥
ማንም ቤዛውን#49፥8 የሕይወት ዋጋውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥
9የነፍሳቸው ዋጋ ክቡር ነው፥
መቼውንም በቂ አይሆንም፥
10ሰው ገና እንዲኖርና አዘቅቱንም እንዳያይ
11 #
መዝ. 39፥7፤ መክ. 2፥16፤ ሲራ. 11፥18-19። ጠቢባን እንደሚሞቱ፥
ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንደሚጠፉ፥
ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንደሚተዉ አይቶአል።
12ብዙ መሬት በስማችው ቢያስጠሩም እንኳን፥
መቃብራቸው የዘለዓለም ቤታቸው፥ ለልጅ ልጅ የሚሆን ማደሪያቸውም ነው።
13 #
መክ. 3፥18-21። ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፥
እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።
14ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥
ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በንግግራቸው ይደሰታሉ።
15እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥
እረኛቸውም ሞት ነው፥
ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥
ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።
16 #
መዝ. 16፥10፤ 86፥13፤ 103፥4፤ 116፥8። ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና
ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።
17የሰው ሀብት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥
18 #
ሲራ. 11፥18-19፤ መክ. 5፥15፤ 1ጢሞ. 6፥7። በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥
ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።
19በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና#49፥19 አስደስቶአልና
ለሰውነቱ መልካም በማድረጉ ይወደሳልና።
20 #
ኢዮብ 10፥21-22። ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፥
ለዘለዓለም ብርሃንን ወደ ማያዩበት።
21አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው
እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 49: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ