የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 40

40
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # ሰቆ.ኤ. 3፥25። በትዕግሥት ጌታን ደጅ ጠናሁት፥
እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።
3 # መዝ. 28፥1፤ 30፥4፤ 69፥3፤15-16፤ 88፥5፤ ምሳ. 1፥12፤ ዮናስ 2፥7። ከጥፋት ጉድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥
እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
4 # መዝ. 33፥3። አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፥
ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥
በጌታም ይታመናሉ።
5 # መዝ. 1፥1፤ ምሳ. 16፥20፤ ኤር. 17፥7። ጌታን የታመነ
ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
6 # መዝ. 35፥10፤ መዝ. 71፥15፤ 139፥17-18። አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥
አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፥
ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።
7 # ዕብ. 10፥5-7፤ መዝ. 51፥18-19፤ አሞጽ 5፥22፤ ሆሴዕ 6፥6፤ ኢሳ. 1፥11-15። መሥዋዕትንና ቁርባንን አልወደድህም፥
የሚሰማ ጆሮ ሰጠኸኝ፥
የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም።
8በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፥
ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፥
9 # መዝ. 37፥31። አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”
10 # መዝ. 22፥23፤ 26፥12፤ 35፥18፤ 149፥1። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አበሠርሁ፥
እነሆ፥ ከንፈሮቼን አላግድም፥
አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ።
11አዳኝ ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሰወርኩም፥
ታማኝነትህንና ማዳንህንም ተናገርሁ፥
ጽኑ ፍቅርህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።
12 # መዝ. 89፥34። አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥
ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።
13 # መዝ. 38፥5፤ 11፤ ዕዝ. 9፥6። ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፥
ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል
ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
14 # መዝ. 70፥2-6፤ 71፥12። አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፥
አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
15 # መዝ. 35፥4፤26። ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥
በአንድነትም ይዋረዱ፥
በእኔ ላይ ክፋትን ሊያደርጉ የሚወድዱ
ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይጐስቁሉም።
16 # መዝ. 35፥21፤25። እሰይ እሰይ የሚሉኝ
እፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ።
17 # መዝ. 35፥27። አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ
በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፥
ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ
ዘወትር፦ ጌታ ታላቅ ይሁን ይበሉ።
18እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥
ጌታ ግን ያስብልኛል፥
አንተ ረዳቴና አዳኜ ነህ፥
አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ