የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 36

36
1ለመዘምራን አለቃ፥ የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር።
2 # ሮሜ 3፥18። ኃጢአተኛ በራሱ የሚያስት ነገርን ይናገራል፥
የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዐይኖቹ ፊት የለም።
3እራሱን ሸንግሎአልና፥
ኃጢአቱን መቀበልና መጥላት ይሳነዋል።
4የአፉ ቃል ግፍና ሽንገላ ነው፥
ማስተዋልን በጎ ማድረግንም ተወ።
5 # ሚክ. 2፥1። በመኝታው ጠማማነትን አሰበ፥
መልካም ባልሆነች መንገድ ቆሞአል፥
ክፋትን አይቃወማትም።
6 # መዝ. 57፥11፤ 71፥19። አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ነው፥
ታማኝነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች።
7ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች፥
ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት፥
አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።
8 # መዝ. 17፥8። አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ!
የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።
9 # ዘፍ. 2፥8፤ 10። ከቤትህ ሙላት ይጠግባሉ፥
ከተድላህም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ።
10 # መዝ. 80፥4፤ 8፤ 20፤ ኢሳ. 55፥1፤ ዮሐ. 4፥14። የሕይወት ምንጭ በአንተ ዘንድ ነውና፥
በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
11ጽኑ ፍቅርህን በሚያውቁህ ላይ፥
ጽድቅህንም ልባቸው በቀና ላይ ዘርጋ።
12የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥
የዐመጸኞችም እጅ አያስተኝ።
13ዓመፃን የሚያደርጉ ሁሉ ከዚያ ወደቁ፥
ወድቀዋል፥ መቆምም አይችሉም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ