መዝሙረ ዳዊት 28
28
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 18፥2፤ መዝ. 30፥4፤ 88፥5፤ 143፥7፤ ምሳ. 1፥12። አቤቱ፥ ወደ አንተ እጠራለሁ፥
ዝም ብትለኝ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል፥
አንተ ዓለቴ ሆይ፥ ዝም አትበለኝ።
2 #
መዝ. 134፥2። ወደ መቅደስህ ማደሪያ እጄን ባነሣሁ ጊዜ፥
ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
3 #
መዝ. 26፥9፤ መዝ. 12፥2፤ 55፥22፤ 62፥5፤ ምሳ. 26፥24-28። ከኃጥኣንና ከክፉ አድራጊዎች ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፥
ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላም ከሚናገሩት ጋር አትጣለኝ።
4 #
2ሳሙ. 3፥39፤ ራእ. 22፥12። እንደ ሥራቸው እንደ አካሄዳቸውም ክፋት ስጣቸው፥
እንደ እጃቸውም ሥራ ስጣቸው፥
ፍዳቸውን ወደ ራሳቸው መልስ።
5 #
ኢሳ. 5፥12። ወደ ጌታ ሥራ
ወደ እጆቹም አደራረግ አላሰቡምና
ያፈርሳቸዋል እንጂ አይሠራቸውም።
6የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና
ጌታ ይመስገን።
7ጌታ ኃይሌና ጋሻዬ ነው፥
ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፥
ልቤም ደስ ይለዋል፥
ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።
8ጌታ ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥
ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው።
9ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥
ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 28: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ