አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፥ በማዳንህም እንዴት አብዝቶ ሐሤትን ያደርጋል! የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም። በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፥ ከንጹሕ ወርቅ የተሠራ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ። ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥ ለረጅም ዘመን ለዘለዓለም ዓለም። በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፥ ሞገስንና ግርማን በላዩ አኖርህ። የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስ ታሰኘዋለህ።
መዝሙረ ዳዊት 21 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 21:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos