መዝሙረ ዳዊት 148:7-14

መዝሙረ ዳዊት 148:7-14 መቅካእኤ

የባሕር አራዊትና ጥልቆችም ሁሉ፥ ጌታን ከምድር አመስግኑት፥ እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥ ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፥ የሚያፈራም ዛፍና ዝግባ ሁሉ፥ አራዊትና እንስሳት ሁሉ፥ የሚሳቡና የሚበርሩ ወፎችም፥ የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥ አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥ ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፥ የጌታን ስም ያመስግኑ፥ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥ ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው። የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ።