የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 148

148
1ሃሌ ሉያ።
ጌታን ከሰማያት አመስግኑት፥
በአርያም አመስግኑት።
2 # መዝ. 103፥20፤ ዳን. 3፥58-63። መላእክቱ ሁሉ፥ አመስግኑት፥
ሠራዊቱ ሁሉ፥ አመስግኑት።
3ፀሐይና ጨረቃ፥ አመስግኑት፥
የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ፥ አመስግኑት።
4ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥
ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ።
5 # መዝ. 33፥9፤ ዘፍ. 1፥3፤ ዮዲ. 16፥14። የጌታን ስም ያመስግኑት፥
እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ።
6ለዘለዓለም ዓለም አቆማቸው፥
ትእዛዝን ሰጠ፥ አያልፉትምም።
7 # መዝ. 135፥6፤ ዘፍ. 1፥21። የባሕር አራዊትና ጥልቆችም ሁሉ፥
ጌታን ከምድር አመስግኑት፥
8እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥
ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥
9 # ኢሳ. 44፥23። ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፥
የሚያፈራም ዛፍና ዝግባ ሁሉ፥
10 # መዝ. 30፥5፤ ዘፍ. 1፥21፤24፤ ዘዳ. 4፥7። አራዊትና እንስሳት ሁሉ፥
የሚሳቡና የሚበርሩ ወፎችም፥
11የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥
አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥
12ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥
ሽማግሌዎችና ልጆች፥
13 # መዝ. 30፥5፤ ዘዳ. 4፥7። የጌታን ስም ያመስግኑ፥
ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥
ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው።
14የሕዝቡንም ቀንድ#148፥14 ኃይል ከፍ ከፍ ያደርጋል፥
የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና
ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ሃሌ ሉያ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ