መዝሙረ ዳዊት 125
125
1የዕርገት መዝሙር።
#
ምሳ. 10፥25። በጌታ የታመኑ
እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር
እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
2 #
ዘዳ. 32፥11። ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፥
ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም
ጌታ በሕዝቡ ዙሪያ ነው።
3ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ
የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም።
4 #
መዝ. 18፥25። አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
5 #
መዝ. 128፥6፤ ምሳ. 3፥32። ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን
ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል።
ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 125: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ