መዝሙረ ዳዊት 124

124
1የዳዊት የዕርገት መዝሙር።
# መዝ. 129፥1። ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን
እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን
ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3 # ምሳ. 1፥12። ቁጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፥
በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፥
4 # መዝ. 18፥5፤ 69፥2። በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥
በነፍሳችንም ላይ ወራጅ ውኃ ባለፈ ነበር፥
5በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
6ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን ጌታ ይመስገን።
7ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፥
ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
8 # መዝ. 121፥2፤ 146፥6። ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ
በጌታ ስም ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ