ሃሌ ሉያ! ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ፥ ጌታ የታደጋቸው፥ ከጠላትም እጅ ያዳናቸው ይናገሩ። ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከባሕር፥ ከየአገሩ ሰበሰባቸው። በበረሃ፥ በምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፥ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም። ተራቡ፥ ተጠሙም፥ ነፍሳቸውም ዛለች። በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፥ ወደሚኖሩበት ከተማ ይሄዱ ዘንድ በቀና መንገድን መራቸው። ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥ የተጠማችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራበችን ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።
መዝሙረ ዳዊት 107 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 107:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos