መጽሐፈ ምሳሌ 9
9
1ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥
ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።
2ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን አዘጋጀች#9፥2 በወይን ጠጁ ውስጥ የተለያዩ ቅመሞችን ጨመረች።፥
ማዕድዋን አሰናዳች።
3ሴቶች አገልጋዮችዋን ልካ
በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች፦
4“አላዋቂ የሆነ በዚህ በኩል ይለፍ፥”
አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ አለች፦
5“ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥
ያጣፈጥኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
6አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥
በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”
7ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥
ክፉንም የሚዘልፍ ኃፍረት ይገጥመዋል።
8ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፥
ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።
9ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ይበልጡን ጠቢብ ይሆናል፥
ጻድቅንም አስተምረው፥ ይበልጡን አዋቂ ይሆናል።
10 #
ኢዮብ 28፥28፤ መዝ. 111፥10፤ ምሳ. 1፥7። የጥበብ መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥
ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።
11ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥
የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና።
12ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥
ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ።
(የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።)
ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥
ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ።
ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥
የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል።
የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥
የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥
ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥
ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥
የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።
13አላዋቂ ሴት ሁከተኛ ናት፥
አሳብ የላትም፥ አንዳችም አታውቅም።
14በቤትዋ ደጅ
በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ በወንበር ላይ ትቀመጣለች፥
15በመንገድ የሚያልፉትን
አካሄዳቸውንም ያቀኑትን ለመጥራት፦
16“አላዋቂ የሆነ በዚያ ይለፍ፥”
አእምሮ የጐደለውንም እንዲህ አለች፦
17“የስርቆት ውኃ ይጣፍጣል፥
የተሸሸገም እንጀራ#9፥17 ተደብቀው የሚበሉት እንጀራ። ደስ ያሰኛል።”
18ነገር ግን እርሱ ሙታን ከዚያ እንዳሉ፥
ተጋብዦችዋም በሲኦል ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ አያውቅም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 9: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ