መጽሐፈ ምሳሌ 6:23-29

መጽሐፈ ምሳሌ 6:23-29 መቅካእኤ

ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥ ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ከሌላይቱም ሴት አታላይ ምላስ። ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥ በዐይኖችዋም አትማረክ። የሴተኛ ዐዳሪዋ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፥ አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች። በጉያው እሳትን የሚታቀፍ፥ ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው? በፍም ላይ የሚሄድ እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው? ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።