እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን፣ የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤ እርሷም ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ ልዝብ አንደበት ካላት ባዕድ ሴት ትጠብቅሃለች። ውበቷን በልብህ አትመኝ፤ በዐይኗም አትጠመድ። ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች። ለመሆኑ ልብሱ ሳይቃጠል፣ በጕያው እሳት መያዝ የሚችል ሰው አለን? አንድ ሰው እግሮቹ ሳይቃጠሉ፣ በፍም ላይ መሄድ ይችላልን? ከሰው ሚስት ጋራ የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤ የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም።
ምሳሌ 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ምሳሌ 6
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ምሳሌ 6:23-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች