የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 4:20-27

መጽሐፈ ምሳሌ 4:20-27 መቅካእኤ

ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሎቼም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃቸው፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው። ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። ከሁሉ አስበልጠህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት ምንጭ እርሱ ነውና። ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፥ አሳሳች ቃሎችን ከአንተ አርቅ። ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ። የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፥ እግርህንም ከክፉ መልስ።