መጽሐፈ ምሳሌ 29
29
1ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥
ፈውስም የለውም።
2ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፥
ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።
3ጥበብን የወደደ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፥
አመንዝሮችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያጠፋል።
4ንጉሥ በፍትሕ አገሩን ያጸናል፥
ጥቅም የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል።
5ወዳጁን በሽንገላ የሚናገር ሰው
ለእግሩ ወጥመድን ይዘረጋል።
6ክፉ ሰው በጥፋቱ ይጠመዳል፥
ጻድቅ ግን ደስ ይለዋል፥ እልልም ይላል።
7ጻድቅ የድሆችን መብት ይመለከታል፥
ክፉ ሰው ግን ይህንን አያስተውልም።
8ፌዘኞች ከተማቸውን ያቃጥላሉ፥
ጠቢባን ግን ቁጣን ያስቀራሉ።
9ጠቢብ ከሞኝ ጋር ቢጣላ፥
ሞኙ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ዕረፍትም አይኖርም።
10ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ንጹሑን ሰው ይጠላሉ፥
እንዲሁም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።
11ሞኝ ሰው ቁጣውን ሁሉያለችግር ያወጣል፥
ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።
12አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥
ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።
13ድኀና ግፈኛ ተገናኙ፥
ጌታ የሁለቱንም ዐይን ያበራል።
14ለድሀ በእውነት የሚፈርድ ንጉሥ፥
ዙፋኑ ለዘለዓለም ይጸናል።
15በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፥
ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
16ክፉ ሰዎች ሥልጣን ሲይዙ ሕግ መጣስ ይበዛል፥
ጻድቃን ግን ውደቀታቸውን ያያሉ።
17ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፥
ለነፍስህም ደስታን ይሰጣታል።
18ራእይ ከሌለ ሕዝብ ከመስመር ይወጣል፥
ሕግን የሚጠብቅ ግን ብፁዕ ነው።
19 #
ሲራ. 33፥25-30። አገልጋይ በቃል ብቻ አይገሠጽም፥
ቢያስተውል እንኳ አይመልስምና።
20በችኮላ የሚናገረውን ሰው አየኸውን?
ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው።
21ባርያውን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማቀማጠል የሚያሳድግ
የኋላ ኋላ እንደ ጌታ ያደርገዋል።
22ቁጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል።
ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።
23ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፥
መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።
24ከሌባ ጋር የሚካፈል ነፍሱን ይጠላል፥
መርገምን ይሰማል፥ ነገር ግን ምንም አይገልጥም።
25ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፥
በጌታ የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።
26ብዙ ሰዎች የሹምን ፊት ይሻሉ፥
የሰው ፍርድ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።
27ኃጢአተኛ በጻድቃን ዘንድ አስጸያፊ ነው፥
በቀና መንገድ የሚሄደውም በኀጥኣን ዘንድ አስጸያፊ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 29: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ