መጽሐፈ ምሳሌ 21
21
1የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥
ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።
2የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፥
ጌታ ግን ልብን ይመዝናል።
3ጌታ ከመሥዋዕት ይልቅ
ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል።
4ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው።
5የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥
ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል።
6በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፥
ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።
7ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና
የኀጥኣን ንጥቂያ ራሳቸውን ያጠፋቸዋል።
8የበደለኛ መንገድ የጠመመች ናት፥
የንጹሕ ሥራ ግን የቀና ነው።
9 #
ሲራ. 25፥16። ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ
በውጪ በቤት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
10የኀጥእ ነፍስ ክፉን ትመኛለች፥
በፊቱም ባልንጀራው ሞገስን አያገኝም።
11ፌዘኛ ቅጣትን በተቀበለ ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፥
ጠቢብም ቢማር እውቀትን ይቀበላል።
12ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥
ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።
13የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥
እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።
14ስጦታ በስውር ቁጣን ታጠፋለች፥
የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቁጣን ታበርዳለች።
15ፍርድን ማድረግ ለጻድቅ ደስታ ነው፥
ኃጢአትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው።
16ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው
በሙታን ጉባኤ ያርፋል።
17ተድላ የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥
የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድድ ሀብታም አይሆንም።
18ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፥
በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።
19ከጠበኛና ከቁጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ
በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
20የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፥
አእምሮ የሌለው ሰው ግን ያሟጥጠዋል።
21ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል
ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።
22ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥
የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል።
23አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ
ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።
24ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥
እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል።
25ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥
እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
26ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፥
ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም።
27 #
ሲራ. 7፥9። የክፉዎች መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፥
ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው።
28ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፥
የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል።
29ኀጥእ ፊቱን ያጠነክራል፥
ቅን ሰው ግን መንገዱን ያጸናል።
30ያለ ጌታ የሚሠምር፥
ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።
31ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፥
ድል ግን ከጌታ ዘንድ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 21: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ