መጽሐፈ ምሳሌ 1
1
1 #
1ነገ. 4፥32። የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፥
2ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥
የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፥
3የጥበብን ትምህርት
ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንም ለመቀበል፥
4ብልሃትን ለአላዋቂዎች ለመስጠት
ለወጣቶችም እውቀትንና ጥንቃቄን፥
5ጠቢብ እነዚህን በመስማት ዐዋቂነትን ይጨምራል፥
አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።
6ምሳሌንና ምሥጢርን
የጠቢባንን ቃልና ዕንቆቅልሸ ለማስተዋል።
7 #
ኢዮብ 28፥28፤ መዝ. 111፥10፤ ምሳ. 9፥10፤ ሲራ. 1፥14። የዕውቀት#1፥7 ሰባ ሊቃናት (ግሪኩ) “የጥበብ መጀመሪያ” ይላል። መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥
ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
8ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥
የእናትህንም ሕግ አትተው፥
9ለራስህ የሞገስ ዘውድ
ለአንገትህም ሐብል ይሆንልሃልና።
10ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።
11ደምን ለማፍሰስ “ና እናድባ፥
ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት” ቢሉ፥
12“በሙሉ ሕይወት እያሉ፥ ከነነፍሳቸው፥ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥
ወደ ጉድጓድ እንደሚወድቁም ይሁኑ፥
13መልካምና ውድ ሀብት ሁሉ እናገኛለን፥
ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን፥
14ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፥
ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ”፥
15ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥
ከጎዳናቸውም እግርህን አርቅ፥
16እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥
ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።
17ወጥመድ በወፎች ዐይን ፊት በከንቱ ይተከላልና።
18እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥
በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ።
19በግፍ ማትረፍ የሚፈልግ ሁሉ መንገዱ እንዲሁ ነው።
የግፉ ባለቤትም ነፍስ ይነጠቃል።
20 #
ምሳ. 8፥1-3። ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፥
በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፥
21ግርግር ባለበት አደባባይ ትጣራለች፥
በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች፦
22“እናንት አላዋቂዎች፥ እስከ መቼ አላዋቂነት ትወድዳላችሁ?
ፌዘኞችም ፌዝን ይፈቅዳሉ?
ሞኞችም እውቀትን ይጠላሉ?
23ወደ ዘለፋዬ ተመለሱ፥
እነሆ፥ መንፈሴን አፈስስላችኋለሁ#1፥23 ለሚሰማት ጥበብ እንደ ውሃ ምንጭ ሆና ቅን መንገድን ታስተምራለች።፥
ቃሌን አስተምራችኋለሁ።
24በጠራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁ፥
እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ስላላስተዋለ፥
25ምክሬን ሁሉ ግን ችላ ስላላችሁ፥
ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፥
26እኔም በእናንተ መጥፋት እስቃለሁ፥
ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ
27ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በደረሰባችሁ ጊዜ፥
ጥፋታችሁም እንደ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ፥
ጭንቅና መከራ በወረደባችሁ ጊዜ።
28የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥
ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።
29እውቀትን ጠልተዋልና፥
ጌታንም መፍራት አልመረጡምና፥
30ምክሬን አልፈቀዱምና፥
ተግሣጼንም ሁሉ ንቀዋልና፥
31ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥
የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ።
32አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥
ሞኞችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና።
33የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥
ከክፉም ሥጋት ያርፋል።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ