1
መጽሐፈ ምሳሌ 1:7-8
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፥
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 1:32-33
አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሞኞችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና። የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥ ከክፉም ሥጋት ያርፋል።”
3
መጽሐፈ ምሳሌ 1:5
ጠቢብ እነዚህን በመስማት ዐዋቂነትን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 1:10
ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 1:1-4
የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፥ ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፥ የጥበብን ትምህርት ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንም ለመቀበል፥ ብልሃትን ለአላዋቂዎች ለመስጠት ለወጣቶችም እውቀትንና ጥንቃቄን፥
6
መጽሐፈ ምሳሌ 1:28-29
የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። እውቀትን ጠልተዋልና፥ ጌታንም መፍራት አልመረጡምና፥
Home
Bible
Plans
Videos