የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍልቊ 4

4
የቀዓት ወገኖች
1ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 2“ከሌዊ ልጆች መካከል የቀዓትን ልጆች በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ላይ የሕዝብ ቈጠራ አድርግ፤ 3ዕድሜው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያለውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገባውን ሁሉ ትቈጥራለህ። 4በመገናኛው ድንኳን በንዋየ ቅድሳቱ ዘንድ የቀዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤ 5ሰፈሩ ለመጓዝ በተነሣ ጊዜ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚሸፍነውን መጋረጃ ያውርዱ፥ የምስክሩንም ታቦት ይሸፍኑበት፤ 6በእርሱም ላይ የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። 7በተቀደሰው ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ሙዳዮችንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለመጠጥ ቁርባንም መንቀሎቹን ያስቀምጡበት፤ ሁልጊዜም የሚቀርበው እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን። 8በእነርሱም ላይ ቀይ መጐናጸፊያ ይዘርጉ፥ በአስቆጣውም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። 9ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ 10መቅረዙንና የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያኑሩት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። 11በወርቁም መሠዊያ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። 12በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው። 13አመዱንም ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፥ ሐምራዊውንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ 14በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። 15አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸፈናቸውን በጨረሱ ጊዜ፥ ሰፈሩም ለመጓዝ ሲነሣ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ከዚያም በኋላ ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። የቀዓት ልጆች የሚሸከሙአቸው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች እነዚህ ናቸው።
16“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።”
17ጌታ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 18“የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤ 19ነገር ግን እጅግ ቅዱስ ወደ ሆኑት ነገሮች በቀረቡ ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲህ አድርጉላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ እያንዳንዱንም ሰው በየተግባሩና በየሥራው ጫና ይመድቡት፤ 20ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋየ ቅድሳቱን ለአንድ አፍታ እንኳ ለማየት አይግቡ።”
የጌድሶናውያን ወገኖች እና የሜራሪ ወገኖች
21ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 22“እንዲሁም የጌድሶንን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገኖቻቸውም የሕዝብ ቈጠራ አድርግ። 23በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው። 24የጌድሶናውያን ወገኖች በማገልገልና በመሸከም የሚሰጡት አገልግሎት ይህ ነው፦ 25የማደሪያውን መጋረጆች፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ መደረቢያውን፥ በእርሱም ላይ ያለውን የአቆስጣውን ቁርበት መሸፈኛ፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ 26የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መግብያ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ የሚገለገሉባቸውንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ እነርሱንም በሚመለከት ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ያድርጋሉ። 27የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በየአገልግሎታቸውም የሚደርስባቸውን ሸክም ሁሉ ለእያንዳንዳቸው ትደለድላላችሁ። 28የጌድሶናውያን ወገኖች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ሥራቸውንም የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታማር ይቈጣጠራል።
29“የሜራሪንም ልጆች በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቁጠራቸው። 30በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው። 31በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ የሚሸከሙት፥ የማደሪያውን ሳንቆች፥ መቀርቀሪያዎቹንም፥ ምሶሶዎቹንም፥ እግሮቹንም፥ 32በዙሪያውም የሚቆሙትን የአደባባዩ ምሰሶች፥ እግሮቻቸውንም፥ ካስማዎቻቸውንም፥ አውታሮቻቸውንም፥ ዕቃዎቻቸውንና በተጓዳኝ የሚደረጉላቸውን አገልግሎቶች ሁሉ ነው፤ መሸከምም ያለባቸውን ዕቃዎች በየስሙ ትደለድላላችሁ። 33በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ቁጥጥር ሥር ሆነው በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው።”
በሌዋውያን ላይ የተደረገ የሕዝብ ቈጠራ
34ሙሴና አሮንም የሕቡም አለቆች የቀዓትን ልጆች በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቈጠሩአቸው። 35በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤ 36በየወገኖቻቸውም ከእነርሱ የተቈጠሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ኀምሳ ነበሩ። 37ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከቀዓታውያን ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።
38በየወገኖቻቸውም በየአባቶቻቸውም ቤቶች የተቈጠሩት የጌድሶን ልጆች፥ 39በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የገቡት፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥ 40በየወገኖቻቸውም በየአባቶቻቸውም ቤቶች የተቈጠሩት ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ ነበሩ። 41ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከጌድሶን ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።
42በየወገኖቻቸውም በየአባቶቻቸውም ቤቶች ከሜራሪ ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ 43በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የገቡት ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥ 44በየወገኖቻቸው የተቈጠሩት ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 45ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ ከሜራሪ ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።
46በየወገኖቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች ከሌዋውያን የተቈጠሩት ሁሉ፥ ሙሴና አሮን የእስራኤልም አለቆች የቈጠሩአቸው፥ 47በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራውን ለመሥራትና ዕቃውን ለመሸከም የገቡት ሁሉ፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥ 48ከእነርሱ የተቈጠሩት ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ። 49እንደ ጌታ ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ ተደለደሉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ