የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ 11

11
የከተማዋ የሕዝብ ቍጥር መጨመር
1 # ነህ. 7፥4። የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ። 2ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በፈቃደኝነት ራሳቸውን የሰጡትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።
3 # 1ዜ.መ. 9፥2-34። በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ። 4ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፦ ከፋሬስ#11፥4 ዕብራይስጡ “ፓሬጽ” ይለዋል። ልጆች የማሃላልኤል ልጅ፥ የሽፋጥያ ልጅ፥ የአማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዑዚያ ልጅ ዓታያ፤ 5የሺሎናዊው ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የሐዛያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ ማዓሤያ። 6በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ኃያላን ነበሩ።
7የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የይሻዕያ ልጅ፥ የኢቲኤል ልጅ፥ የማዓሤያ ልጅ፥ የቆላያ ልጅ፥ የፕዳያ ልጅ፥ የዮዔድ ልጅ የምሹላም ልጅ ሳሉ። 8ከእርሱም በኋላ ጋባይ፥ ሳላይ፥ ዘጠኝ መቶም ሀያ ስምንት። 9አለቃቸውም የዚክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማው ላይ ሁለተኛ የተሾመ ነበረ።
10ከካህናቱ፦ የዮያሪብ ልጅ ይዳዕያ፥ ያኪን፥ 11የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአሒጡብ ልጅ የምራዮት ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ የምሹላም ልጅ፥ የሒልቂያ ልጅ ሥራያ፥ 12የቤቱን ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሀያ ሁለት፤ የማልኪያ ልጅ፥ የፓሽሑር ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የአምጺ ልጅ፥ የፍላልያ ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፥ 13ወንድሞቹ የአባቶች መሪዎች ሁለት መቶ አርባ ሁለት፤ የኢሜር ልጅ፥ የምሺሌሞት ልጅ፥ የአሕዛይ ልጅ፥ የዓዛርኤል ልጅ ዓማሽሳይ፥ 14ወንድሞቻቸው መቶ ሀያ ስምንት ጽኑዓን ኃያላን፤ አለቃቸውም የሃግዶሊም ልጅ ዛብዲኤል ነበረ።
15ከሌዋውያንም የቡኒ ልጅ፥ የሐሻብያ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የሐሹብ ልጅ ሽማዕያ፤ 16ከእግዚአብሔር ቤት በውጭ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሻብታይና ዮዛባድ፤ 17ምስጋናውን በጸሎት ለመጀመር መሪ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የነበረው ባቅቡቅያ፤ የይዱቱን ልጅ፥ የጋላል ልጅ፥ የሻሙዓ ልጅ ዓብዳ። 18በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ።
19በር ጠባቂዎቹ፥ ዓቁብ፥ ጣልሞንና በሮቹን የሚጠብቁ ወንድሞቻቸው፥ አንድ መቶ ሰባ ሁለት ነበሩ። 20ከእስራኤል የቀሩት ካህናቱና ሌዋውያኑ እያንዳንዱ በየርስቱ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ነበሩ። 21የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹም በዖፌል ተቀመጡ፤ ጺሓና ጊሽፓ በቤተ መቅደስ አገልጋዮች ላይ አለቆች ነበሩ።
22 # 2ዜ.መ. 20፥14። በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሓሻብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ዑዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ። 23ስለ እነርሱ የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ የመዘምራኑም ሥርዓት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ። 24ከይሁዳ ልጅ ከዜራሕ ወገኖች የምሼዛቤል ልጅ፥ ፕታሕያ ሕዝቡን በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ።
ከኢየሩሳሌም ውጭ ያሉ መንደሮች
25በሜዳዎቻቸው ስለ ነበሩ ስለ መንደሮቻቸው፦ ከይሁዳ ልጆች አንዳንዶቹ በእነዚህ ቦታዎች ተቀመጡ፦ በቂርያት አርባዕና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋ፥ በይቃብጽኤልና በመንደሮችዋ፥ 26በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤት ጳሌጥ፥ 27በሓጻር ሹዓል፥ በቤርሳቤህና#11፥27 ዕብራይስጡ “ብኤር ሼባዕ” ይለዋል። በመንደሮችዋ 28በጺቅላግ፥ በምኮናና በመንደሮችዋ፥ 29በዔን ሪሞን፥ በጻርዓና ያርሙት፥ 30ዛኖሓ፥ ዓዱላምና በመንደሮቻቸው፥ ላኪሽና ሜዳዎችዋ፥ ዓዚቃና በመንደሮችዋ፤ እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። 31የብንያምም ልጆች ከጋባዕ ጀምሮ በሚክማስ፥ ዓያ፥ ቤትኤልና በመንደሮችዋ፥ 32ዓናቶት፥ ኖብ፥ አናንያ፥ 33ሐጾር፥ ራማ፥ ጊታይም፥ 34ሐዲድ፥ ጽቦዒይም፥ ንባልጥ፥ 35ሎድና በእጀ ጠቢባን ሸለቆ በኦኖ ተቀመጡ። 36በይሁዳ ከነበሩ ከሌዋውያን አንዳንድ ክፍሎች ወደ ብንያም ሆኑ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ