የማርቆስ ወንጌል 2:1-8

የማርቆስ ወንጌል 2:1-8 መቅካእኤ

ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ፤ በቤት ውስጥ እንዳለም ተሰማ። ሰዎች ከበሩ ውጭ ያለው ስፍራ እንኳን እስኪጠባቸው ድረስ ተሰበሰቡ፤ እርሱም ቃሉን ይነግራቸው ነበር። አራት ሰዎችም አንድ ሽባ ሰው ተሸክመው አመጡለት። ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ ማቅረብ ስላልቻሉ፥ እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፤ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፤” አለው። በዚያም ተቀምጠው ከነበሩ አንዳንድ ጻሐፍት በልባቸውም “ይህ ሰው ስለምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል፤” ብለው አሰቡ። ኢየሱስም በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ ወዲያው አውቆ እንዲህ አላቸው “በልባችሁ ይህን ስለምን ታስባላችሁ?

ተዛማጅ ቪዲዮዎች