ኢየሱስ ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም እንደ ተመለሰ፣ ወደ ቤት መግባቱን ሕዝቡ ሰማ። ስለዚህ ከበሩ ውጭ እንኳ ሳይቀር ስፍራ እስኪታጣ ድረስ ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ሰበከላቸው። ሰዎችም አንድ ሽባ በአራት ሰዎች አሸክመው ወደ እርሱ አመጡ። ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ እርሱ ወዳለበት ሊያቀርቡት ስላልቻሉ፣ የቤቱን ጣራ እርሱ ባለበት በኩል ነድለው ቀዳዳ በማበጀት ሽባው የተኛበትን ዐልጋ በዚያ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው። በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ ጸሐፍት ስለዚህ ነገር በልባቸው እያሰላሰሉ፣ “ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው አሰቡ። ኢየሱስም ወዲያው የሚያስቡትን በመንፈሱ ተረድቶ፣ “ለምን በልባችሁ እንዲህ ታስባላችሁ?
ማርቆስ 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ማርቆስ 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማርቆስ 2:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች