ትንቢተ ሚክያስ መግቢያ
መግቢያ
ሚክያስ በነቢዩ ኢሳይያስ ጊዜ የነበረ ነቢይ ሲሆን፥ ተወላጅነቱም በደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት ውስጥ በምትገኝ በአንዲት የገጠር ከተማ ነበር። አሞጽ በሰሜናዊው መንግሥት ላይ ጥፋት እንደሚደርስ እንደ ተናገረው ሁሉ ሚክያስም በነዚያው ምክንያቶች በይሁዳ መንግሥት ላይ ጥፋት እንደሚደርስ ተንብዮ ነበር። እንዲሁም ይፈጸም በነበረው አስከፊ የሆነ የፍትሕ መጓደል የተነሣ እግዚአብሔር ፍርድን እንደሚያመጣ አስጠንቅቆ ነበር። ይሁን እንጂ የሚክያስ ትንቢት ወደ ፊት መልካም ነገሮች እንደሚመጡ የሚያበሥር ተስፋ በመስጠት ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ እምነቱን እንዲያሳድር ይጋብዛል።
ትንቢተ ሚክያስ በእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ዓለም አቀፋዊ ሰላም እንደሚኖር (ከምዕራፍ 4፥1-4) ያስተምራ፥ ከዳዊት ሥርወ መንግሥት ታላቅ ንጉሥ እንደሚወጣና ለሕዝቡ ሰላምን እንደሚሰጥ (ከምዕራፍ 5፥2-4) ያስተምራል። እንዲሁም የእስራኤል ነቢያት የተናገሩት ቃል ሁሉ በአንዲት ጥቅስ እንደሚጠቃለል ይገልጻል። ያቺም ጥቅስ፦
“እርሱ ከእኛ የሚፈልገው ትክክል የሆነውን ነገር እንድናደርግ፥ ደግነት የተሞላበትን ፍቅር እንድናሳይና ከአምላካችን ጋር በፍጹም ትሕትና እንድንራመድ ነው” (6፥8) የምትለዋ ናት።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ጌታ ሕዝቡን ይቀጣል (1፥1-16)
የወደፊት ተስፋ (2፥1-13)
እግዚአብሔር ክፉ መሪዎችንና ሐሰተኞች ነቢያትን ይቀጣል (3፥1-12)
በአዲሲትዋ እስራኤል አዲስ ቤተ መቅደስ (4፥1—5፥14)
የእስራኤል በደለኛነት መገለጡ (6፥1—7፥7)
የሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር መመለስ (7፥8-20)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ትንቢተ ሚክያስ መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ