በነጋም ጊዜ ሊቃነ ካህናትና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለሊቃነ ካህናቱና ለሽማግሌዎቹ መለሰላቸው፤ እንዲህም አለ “ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ።” እነርሱ ግን “ታዲያ እኛ ምን አገባን? ጉዳዩ የራስህ ነው፤” አሉት። ብሩን በቤተ መቅደስ ጥሎ ወጣ፤ ሄዶም ታንቆ ሞተ። ሊቀ ካህናቱም ብሩን አንሥተው “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ። ተማክረውም ለእንግዶች የመቃብር ስፍራ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት። በዚህም ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተብሎ ይጠራል። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረው ተፈጸመ “ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ወሰዱ፤ ጌታም እንዳዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት።”
የማቴዎስ ወንጌል 27 ያንብቡ
ያዳምጡ የማቴዎስ ወንጌል 27
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማቴዎስ ወንጌል 27:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos