የማቴዎስ ወንጌል 27
27
ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት እንደ ቀረበ
(ማር. 15፥1፤ ሉቃ. 23፥1-2፤ ዮሐ. 18፥28-32)
1በነጋም ጊዜ ሊቃነ ካህናትና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤ 2አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።
የአስቆሮቱ ይሁዳ መሞት
(የሐዋ. 1፥18-19)
3 #
የሐዋ. 1፥18፤19። በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለሊቃነ ካህናቱና ለሽማግሌዎቹ መለሰላቸው፤ 4እንዲህም አለ “ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ።” እነርሱ ግን “ታዲያ እኛ ምን አገባን? ጉዳዩ የራስህ ነው፤” አሉት። 5ብሩን በቤተ መቅደስ ጥሎ ወጣ፤ ሄዶም ታንቆ ሞተ። 6ሊቀ ካህናቱም ብሩን አንሥተው “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ። 7ተማክረውም ለእንግዶች የመቃብር ስፍራ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት። 8በዚህም ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተብሎ ይጠራል። 9#ዘካ. 11፥12፤13።በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረው ተፈጸመ
“ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ የገመቱትን፥
የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ወሰዱ፤
10ጌታም እንዳዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት።”
ጲላጦስ ኢየሱስን እንደመረመረው
(ማር. 15፥2-5፤ ሉቃ. 23፥3-5፤ ዮሐ. 18፥33-38)
11ኢየሱስ በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም “አንተ አልህ” አለው። 12በሊቃነ ካህናትና በሽማግሌዎች ሲከሰስ ምንም አልመለሰም። 13በዚያን ጊዜ ጲላጦስ “ስንት ነገር እንደሚመሰክሩብህ አትሰማምን?” አለው። 14እርሱ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰለትም፤ በዚህም ገዢው እጅግ ተደነቀ።
ኢየሱስ የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደበት
(ማር. 15፥6-15፤ ሉቃ. 23፥13-25፤ ዮሐ. 18፥39—19፥16)
15በዚያ በዓል፥ ገዢው ሕዝቡ የወደደውን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው። 16በዚያን ጊዜ በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። 17ስለዚህ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ “ማንን ልፍታላችሁ ኢየሱስ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው። 18በቅናት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። 19እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት። 20ሊቃነ ካህናቱና ሽማግሌዎቹ ግን በርባን እንዲለቀቅ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፋ ሕዝቡን አግባቡ። 21ገዢውም መልሶ “ከሁለቱ የትኛውን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም “በርባንን” አሉ። 22ጲላጦስም “ታዲያ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ። 23እርሱም “ምን ክፉ ነገር ሠራና?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።
24 #
ዘዳ. 21፥6-9። ጲላጦስም ይህ ነገር ሁከት ከማስነሳት በስተቀር ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ፥ ውሃ ወስዶ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ጉዳዩ የእናንተ ነው፤” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። 25ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ። 26በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።
ወታደሮች በኢየሱስ ላይ እንዳፌዙ
(ማር. 15፥16-20፤ ዮሐ. 19፥2-3)
27በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ ሰበሰቡ። 28ልብሱንም ገፈው ቀይ ካባ አለበሱት፤ 29የእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ አፌዙበት፤ 30ተፉበት፤ መቃውንም ነጥቀው ራሱን መቱት። 31ከአፌዙበትም በኋላ ካባውን ገፈው የራሱን ልብስ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
የኢየሱስ መሰቀል
(ማር. 15፥21-32፤ ሉቃ. 23፥25-43፤ ዮሐ. 19፥17-27)
32ሲወጡም ስምዖን የሚባል የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉንም እንዲሸከም አስገደዱት። 33ትርጉሙ የራስ ቅል ስፍራ ወደሚባል ጎልጎታ ወደ ተባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ 34#መዝ. 69፥21።ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልፈለገም። 35#መዝ. 22፥18።ከሰቀሉትም በኋላ ልብሶቹን ዕጣ ጥለው ተካፈሉት፤ 36በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። 37የተከሰሰበትንም ምክንያት “ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው” የሚል ጽሑፍ ከራሱ በላይ አኖሩ። 38በዚያን ጊዜ ከእርሱ ጋር ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ አንዱ ደግሞ በግራው ተሰቀሉ። 39#መዝ. 22፥7፤ 109፥25፤ ሲራ. 12፥17፤18፤ 13፥7።በዚያ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበር፤ 40#ማቴ. 26፥61፤ ዮሐ. 2፥19።“ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህሰ እስቲ ከመስቀል ውረድ፤” ይሉት ነበር። 41እንዲሁም ደግሞ ሊቃነ ካህናት፥ ከጻፎችና ከሽማግሌዎች ጋር እያፌዙ እንዲህ አሉት፦ 42“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ነው፤ አሁን ከመስቀል ይውረድና እኛም በእርሱ እናምናለን። 43#መዝ. 22፥8፤ ጥበ. 2፥18-20።በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሏልና የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው።” 44ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም ደግሞ እንዲህ እያሉ ይሰድቡት ነበር።
የኢየሱስ መሞት
(ማር. 15፥33-41፤ ሉቃ. 23፥44-49፤ ዮሐ. 19፥28-30)
45ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። 46#መዝ. 22፥1።በዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ኢየሱስ “ኤሊ ኤሊ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም “አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው። 47በዚያ ቆሙት ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ ሰምተው “ኤልያስን ይጠራል” አሉ። 48#መዝ. 69፥21።ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠና ሰፍነግ ወስዶ የወይን ሆምጣጤ ሞላበት፤ በመቃም አስሮ አጠጣው። 49የተቀሩት ግን “ተወው፤ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ እንይ” አሉ። 50ኢየሱስ እንደገና በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።
51 #
ዘፀ. 26፥31-33። እነሆ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤ 52መቃብሮችም ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው ከነበሩት የብዙ ቅዱሳን በድን ተነሣ፤ 53ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስቷ ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ። 54የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ።
55 #
ሉቃ. 8፥2፤3። ኢየሱስን እያገለገሉት ከገሊላ የተከተሉት፥ በሩቅ ሆነው የሚመለከቱ ብዙ ሴቶች እዚያ ነበሩ፤ 56ከእነርሱም መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያምና የዘብዴዎስ ልጆች እናት ነበሩ።
የኢየሱስ መቀበር
(ማር. 15፥42-47፤ ሉቃ. 23፥50-56፤ ዮሐ. 19፥38-42)
57በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የሚባል ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱም የኢየሱስ ደቀመዝሙር ነበረ፤ 58እርሱም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው፤ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ። 59ዮሴፍም ሥጋውን ወስዶ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፤ 60ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብሩ አኖረው፤ በመቃብሩ በር ላይ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ። 61እዚያም መግደላዊት ማርያምና ሌላይቱ ማርያም በመቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር።
የኢየሱስ መቃብር እንደተጠበቀ
62በማግሥቱም ከመዘጋጀት#27፥62 ቅዳሜ በኋላ፥ ሊቃነ ካህናትና ፈሪሳውያን ከጲላጦስ ጋር ተሰበሰቡ፥ 63#ማቴ. 16፥21፤ 17፥23፤ 20፥19፤ ማር. 8፥31፤ 9፥31፤ 10፥33፤34፤ ሉቃ. 9፥22፤ 18፥31-33።እንዲህም አሉት፦ “ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወት ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ’ እንዳለ ትዝ አለን። 64ስለዚህ ደቀመዛሙርቱ መጥተው እንዳይሰርቁትና ለሕዝቡም ‘ከሙታን ተነሥቶአል’ እንዳይሉ፥ መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ የኋለኛው ስሕተት ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል።” 65ጲላጦስም “ጠባቂዎች አሉላችሁ፤ ሄዳችሁ እንደምታውቁት አስጠብቁ፤” አላቸው። 66ሄደውም መቃብሩን ድንጋዩን በማተም ጠባቂዎች አቆሙ።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 27: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ