መጽሐፈ ኢዮብ 37

37
1“ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥
ከስፍራውም ውጭ ዘለለ።
2የድምፁን መትመም ስሙ፥
ከአፉም የሚወጣውን ጉርምርምታ አድምጡ።
3መብረቁንም ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥
ወደ ምድርም ዳርቻ ይሰድዳል።
4ከበስተኋላው ድምፅ ያገሣል፥
በግርማውም ድምፅ ያንጐደጉዳል፥
ድምፁም በተሰማ ጊዜ
መብረቁን አይከለክልም።
5እግዚአብሔር በአስደናቂ ሁኔታ በድምፁ ያንጐደጉዳል፥
እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
6በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ፦
በምድር ላይ ውደቁ ይላል።
7ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድ
የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል።
8አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥
በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
9ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥
ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።
10ከእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ተሰጥቶአል፥
የውኆችም ስፋት ይጠጥራል።
11የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፥
የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፥
12-13ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረትም ቢሆን፥
ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ
ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ
ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራሉ።
14ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥
ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።
15በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥
የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?
16ወይስ የደመናውን መንሳፈፍ፥
ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?
17በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥
ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
18እንደ ቀለጠ መስተዋት
ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?
19እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና
ለርሱ የምንለውን አስታውቀን።
20ማንም በእርሱ ላይ ቢናገር ፈጽሞ ይዋጣልና
እኔ መናገር እንደምፈልግ መንገር ድፍረት አይሆንምን?
21አሁንም ነፋስ አልፎ ካጠራቸው በኋላ፥
ሰው በሰማያት የሚበራውን ብርሃን ሊመለከት አይችልም።
22ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፥
በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።
23ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፥
በኃይል ታላቅ ነው፥
በፍርድና በጽድቅም ሃብታም ነው፤ አይጨቁንምም።
24ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፥
በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ