የዮሐንስ ወንጌል 19:14-16

የዮሐንስ ወንጌል 19:14-16 መቅካእኤ

የፋሲካም በዓል የሚዘጋጅበት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ፤ አይሁድንም “እነሆ ንጉሣችሁ!” አላቸው። እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱለት እንግዲህ በዚህ ጊዜ ነው እንዲሰቀል አሳልፎ የሰጣቸው። ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤