ኦሪት ዘፍጥረት 11:11-30

ኦሪት ዘፍጥረት 11:11-30 መቅካእኤ

ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ወለደ። አርፋክስድም ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሼላሕንም ወለደ፥ አርፋክስድም ሼላሕን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ፥ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፥ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፥ ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፥ ራግውንም ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፥ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፥ ናኮርንም ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ፥ ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ። የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፥ ሐራንም ሎጥን ወለደ። ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፥ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፥ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፥ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው። ሦራም መካን ነበረች፥ ልጅ አልነበራትም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}