የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሕዝቅኤል 7

7
ሊመጣ የቀረበው ጥፋት
1የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ፍጻሜ! በአራቱም የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል። 3አሁን ፍጻሜ በአንቺ ላይ ነው፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እሰድዳለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ። 4ዓይኔ አይራራልሽም እኔም አላዝንም፤ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በክፋት ላይ ክፋት እነሆ፥ ይመጣል። 6ፍጻሜ መጥቷል፥ ፍጻሜ መጥቷል፥ በአንቺ ላይ ነቅቷል፥ እነሆ፥ መጥቷል። 7በምድር የምትኖር ሆይ፥ ፍጻሜህ ወደ አንተ መጥቷል፥ ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሽብር ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም። 8አሁን በቅርብ መዓቴን በአንቺ ላይ አፈስሳለሁ፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እፈጽማለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ። 9ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
10እነሆ ቀኑ፥ እነሆ መጥቷል፥ ፍጻሜህ መጥቷል፥ ብትሩ አብቧል፥ ትዕቢትም አቆጥቁጦአል#7፥10 ዕንቡጥ ይዟል።11ሁከት ወደ ክፋት ብትርነት አደገ፥ ከእነርሱ፥ ከብዛታቸው፥ ከሀብታቸውም አንድም አይቀርም፥ ከመካከላቸው የሚልቅም የለም። 12ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሚገዛ ደስ አይበለው የሚሸጥም አያልቅስ፥ ቁጣ ብዙዎች#7፥12 ብዙ ሕዝቦች። ሁሉ ላይ ነውና። 13በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጭ ወደሸጠው ነገር አይመለስ፥ ስለ ብዙዎቹ የተነገረው ራእይ አይመለስምና፥ ማንም ሰው በኃጢአቱ ሕይወቱን ማዳን አይችልም።
14መለከቱን ነፍተዋል ሁሉንም ነገር አዘጋጅተዋል፥ ነገር ግን ወደ ጦርነት የሚሄድ የለም፥ ቁጣዬ በብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና። 15ሰይፍ በውጭ፥ ቸነፈርና ራብም ከቤት አለ፥ በሜዳ ያለው በሰይፍ ይሞታል፥ በከተማም ያለውን ቸነፈርና ራብ ይበላዋል#7፥15 ይውጠዋል።16ከእነርሱም የሚሸሹ ያመልጣሉ፥ እንደ ሸለቆ እርግቦች በተራራ ላይ ይሆናሉ፥ ሁሉም በኃጢአታቸው ላይ ያቃስታሉ። 17እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ጉልበቶችም ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳሉ። 18ማቅ ይለብሳሉ፥ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በሁሉም ፊቶች ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውም ሁሉ መላጣ ይሆናል። 19ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ፥ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቆጠራል፥ በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም። አይጠግቡም፥ ሆዳቸውንም አይሞሉም፥ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና። 20የጌጦቻቸውን ውበት ወደ ትዕቢት ለወጡ፥ የርኩሰታቸውን ምስሎችና አስከፊ ነገሮችን ሰሩባቸው፥ ስለዚህ እኔም ይህንን ለእነርሱ ርኩስ ነገር አደርገዋለሁ። 21በባዕድም እጅ ለዝርፊያ፥ በምድር ላሉ ክፉዎች እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እነርሱም ያረክሱአታል። 22ፊቴን ከእነርሱ እመልሳለሁ፥ እነርሱም የተከበረ ቦታዬን ያረክሳሉ፥ ወንበዴዎችም ይገቡባታል ያረክሱአታልም።
23ምድር በደም ፍርድ ተሞልታለች፥ ከተማም በዓመፅ ተሞልታለችና፥ ሰንሰለት ሥራ። 24ከአገሮች ሁሉ ክፉዎችን አመጣለሁ፥ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፥ የኃያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ፥ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ። 25ጭንቀት መጥቷል፥ ሰላምም ይሻሉ፥ አይገኝምም። 26በጥፋት ላይ ጥፋት ይመጣል፥ ወሬም ወሬን ይከተላል፥ ከነቢይ ራእይን ይፈልጋሉ፥ ከካህን ሕግ፥ ከሽማግሌዎችም ምክር ይጠፋል። 27ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ