ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጐ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠረበ፤ በማግስቱም ማልዶ ጌታ እንዳዘዘው ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። ጌታም በደመና ወረደ፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፥ የጌታንም ስም አወጀ። ጌታም በፊቱ አልፎ እንዲህ ብሎ አወጀ፦ “ጌታ፥ ጌታ፥ መሓሪ አምላክ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽ፥ ፅኑ ፍቅሩና እውነቱ የበዛ፥ ፅኑ ፍቅሩን እስከ ሺህ ትውልድ የሚጠብቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በደለኛውን ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆችና በልጅ ልጆች ላይ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ የሚያመጣ አምላክ ነው።” ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተደፍቶ ሰገደ፦
ኦሪት ዘፀአት 34 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 34:4-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos