ወደ ኤፌሶን ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች የጻፈው መልእክት ከሁሉ በፊት የሚያተኲረው “የእግዚአብሔር ዕቅድ የሚፈጸመው በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር የሚሆኑበት ጊዜ ሲደርስ ነው” በሚለው አሳብ ላይ ነው። በተጨማሪም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመተባበር የሰው ዘር ሁሉ አንድ እንዲሆን፥ ይህን ታላቅ ዕቅድ በሥራ ላይ እንዲያውሉት የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያሳስብ ነው።
የኤፌሶን መልእክት በመጀመሪያው ክፍል ጸሐፊው ስለ አንድነት የጀመረውን ርእስ ያስፋፋል። እንደዚሁም እግዚአብሔር አብ ሕዝቡን እንዴት እንደ መረጠ፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የኃጢአታቸውን ይቅርታ እንዴት እንዳገኘና እንዴት እንደ ነጻ ይገልጻል። የእግዚአብሔርም ታላቅ የተስፋ ቃል በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንዴት እንደ ተረጋገጠ ያስረዳል፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ጸሐፊው አንባቢዎቹ በጋራ ሕይወታቸው በክርስቶስ ያላቸው አንድነት እውነተኛ ይሆን ዘንድ እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያሳስባቸዋል።
ሰዎች በክርስቶስ ባላቸው ኅብረት እንዴት አንድ ላይ እንደሚኖሩ በልዩ ልዩ ፈሊጣዊ አነጋገር ተገልጦአል፤ ቤተ ክርስቲያን በአካል ስትመሰል ክርስቶስ ደግሞ የአካሉ ራስ ሆኖ ተመስሏል፤ ቤተ ክርስቲያን በሕንጻ ስትመሰል ክርስቶስ ደግሞ በማእዘኑ ድንጋይ ይመሰላል፤ ቤተ ክርስቲያን በሚስት ስትመሰል ክርስቶስ በባል ይመሰላል። ጸሐፊው በክርስቶስ በኩል የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እጅግ በማድነቅ፥ ሁሉን ነገር የሚመለከተው ከክርስቶስ ፍቅር፥ መሥዋዕትነት፥ ይቅርታ፥ ጸጋና ሰላም አኳያ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-2)
ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን (1፥3—3፥21)
በክርስቶስ አዲስ ሕይወት (4፥1—6፥20)
መደምደሚያ (6፥21-24)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ