ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25-28

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25-28 መቅካእኤ

ባሎች ሆይ! ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ እንደሰጣት፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ ከውሃ መታጠብ ጋር በቃሉ አንጽቶ እንዲቀድሳት፥ እንዲሁም ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር የሌለባት አድርጎ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያንን ለራሱ ሊያቀርባ እንደፈለገ፥ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደገዛ አካላቸው አድርገው ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

ከ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25-28ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች