መጽሐፈ መክብብ መግቢያ

መግቢያ
ይህ መጽሐፍ ሰው በሀብት፥ በዝና፥ በስኬት ወይም በስሜት እርካታ የሕይወትን ትርጉምና ዓላማ በሙላት ማግኘት እንደማይችል በትረካና በምሳሌዎች አማካይነት ይገልጻል። ሰው የጥበብንም ምሥጢር በደንብ እንደማይረዳ፥ ነገር ግን ከሞኝነት መራቅ እንዳለበት ያስተምራል። በመጽሐፉ ከሚደጋገሙ መሪ ሐሳቦች አንዱና ዋነኛው “የከንቱ ከንቱ” የሚለው አባባል ነው (1፥14፤ 2፥11፤ 17፥26)። በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ያለ ማንኛውም ነገር እንደሚለዋወጥ፥ ሊጠፋ እንደሚችል ያመለክታል። “ታዲያ ከጸሐይ በታች፥ የሰው ልጅ ድካም ትርፉ ምን ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ አበክሮ ያቀርባል። እንዲሁም ትንሽ ትርፍ የሚባል ቢገኝ እንኳን ሞት ሁሉንም እኩል እንደሚያደርገው ያወሳል (2፥14-15፤ 19-20)።
መጽሐፈ መክብብ ሰው በሕይወቱ ከመጠን ያለፈ መተማመንና ትምክህት እንዳይኖረው ያስተምራል። ሆኖም ሰው ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን በእግዚአብሔር ስጦታ ሊደሰት እንደሚገባው ያስታውሳል (2፥24፤ 3፥12፤ 5፥17-18፤ 8፥15፤ 9፥7-9፤ 11፥9)።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ ሰው በራሱና በዓለም ከመመካት ይልቅ በእግዚአብሔር፥ በክርስቶስና በዘላለማዊ ሕይወት መመካት እንደሚገባው ለማስተማር አገልግሏል።
መጽሐፍ መክብብን በሚከተለው መንገድ መክፈል ይቻላል፦
የሕይወትን ትርጒም ፍለጋ (1፥1—6፥9)
የሕይወት ትርጒም ድምዳሜ (6፥10—12)
የመልካም ተግባርን መንገዶች ማወቅ አስቸጋሪነት (7፥1—8፥17)
የወደፊቱን ማወቅ አስቸጋሪነት (9፥1—12፥14)
ምዕራፍ

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ