“ጌታም እንዳለኝ፥ ተመልሰን በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፥ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን። ጌታም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ‘በዚህ ተራራማ አገር ለረጅም ጊዜ ተንከራታችኋልና ይብቃችሁ፥ ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ። ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ። የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው። ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፥ ውኃም ደግሞ በገንዘብ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ።’ “ጌታ አምላክህ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፥ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፥ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም።
ኦሪት ዘዳግም 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘዳግም 2:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች