2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 9
9
ዳዊትና መፊቦሼት
1 #
2ሳሙ. 21፥7፤ 1ሳሙ. 18፥1-4፤ 20፥8-10፤15-17፤42። ዳዊትም፥ “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖር ይሆን?” በማለት ጠየቀ። 2#2ሳሙ. 16፥1-4፤ 19፥27።በዚያን ጊዜ ከሳኦል ቤት ጺባ የሚባል አንድ አገልጋይ ስለ ነበር ወደ ዳዊት ጠሩት። ንጉሡም፥ “ጺባ የምትባለው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “አዎን እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ። 3#2ሳሙ. 4፥4።ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም ለንጉሡ፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት። 4#2ሳሙ. 17፥27።ንጉሡም፥ “የት ነው ያለው?” ብሎ ጠየቀ። ጺባም፥ “ሎደባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት። 5ስለዚህም ንጉሥ ዳዊት፥ መፊቦሼትን ከዓሚኤል ከማኪር ቤት ከሎደባር ልኮ አስመጣው። 6የሳኦል ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ። ዳዊትም፥ “መፊቦሼት!” ብሎ ጠራው። እርሱም፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ። 7ዳዊትም፥ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው። 8#1ሳሙ. 24፥15።መፊቦሼት ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፥ “እንደ ሞተ ውሻ ለምቆጠር ለእኔ ይህን ያህል የምታደርግልኝ አገልጋይህ ኧረ ማን ነኝ?” አለ።
9ከዚያም ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ጺባን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “የሳኦልና የቤተሰቡ የሆነውን ሁሉ ለጌታህ የልጅ ልጅ ሰጥቸዋለሁ። 10አንተ፥ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን እረሱለት፥ ምርቱንም አግቡለት። የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ምንጊዜም ከማእዴ ይበላል።” በዚያን ጊዜ ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት። 11#2ሳሙ. 19፥29።ከዚያም ጺባ ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ፥ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፥ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው። ስለዚህም መፊቦሼት እንደ አንዱ ሆኖ ከዳዊት ማእድ ይበላ ነበር። 12#1ዜ.መ. 8፥34።መፊቦሼት ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የጺባ ቤተሰቦች በሙሉ መፊቦሼትን ያገለግሉት ነበር። 13#2ሳሙ. 21፥7።መፊቦሼትም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ።
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 9: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ