2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 12
12
ናታን ዳዊትን ገሠጸው
1 #
ሲራ. 47፥1፤ መዝ. 51። ጌታ ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ሀብታም ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ ድኻ ነበረ። 2ሀብታሙ እጅግ ብዙ በጎችና የቀንድ ከብቶች ነበሩት፤ 3ድኻው ግን ከገዛት ከአንዲት ጠቦት በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም። እየተንከባከበ አብራውም ከልጆቹ ጋር አደገች፤ አብራው ትበላ፤ ከጽዋውም ትጠጣ እንዲሁም በዕቅፉ ትተኛ ነበር፤ ልክ እንደገዛ ልጁ ነበረች። 4ወደ ሀብታሙም ቤት እንግዳ መጣ፤ ሀብታሙ ግን ከራሱ በጎች ወይም ቀንድ ከብቶች ወስዶ ለመጣበት እንግዳ ምግብ ማዘጋጀት አልፈለገም፤ የድኻውን ግልገል ወስዶ ቤቱ ለመጣው እንግዳ አዘጋጀው።” 5ዳዊት በዚያ ሰው ላይ እጅግ ተቆጥቶ ናታንን እንዲህ አለው፤ “ጌታ ምስክሬ ነው! ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል! 6#ዘፀ. 21፥37፤ ሉቃ. 19፥8።እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ባለማዘኑም ስለ ግልገሊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት።” 7#1ሳሙ. 16፥13።ከዚያም ናታን፥ ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለው ይህን ነው፤ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤ 8የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በእቅፍህ አኖርኩ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤትም ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ኖሮ፤ ከዚህ በላይ ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር። 9ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፥ የጌታን ቃል ያቃለልኸው ስለምንድን ነው? ሒታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው። 10#2ሳሙ. 13፥28-29፤ 18፥14።ስለዚህ እኔን አቃለኸኛል፤ ሚስት እንድትሆንህም የሒታዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደሃታልና፥ ሰይፍ ለዘለዓለም ከቤትህ አይርቅም።’ ” 11#2ሳሙ. 16፥21-22።ጌታ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። 12አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህንኑ ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ።” 13#1ነገ. 21፥29፤ መዝ. 32፥5፤ 51፥4፤ ሲራ. 47፥11።ከዚያም ዳዊት ለናታን፥ “ጌታን በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፥ “ጌታ ኃጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤ 14ይህን በመፈጸምህ ግን፥ የጌታ ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፥ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” 15ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፥ የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን ጌታ ከባድ ሕመም ላይ ጣለው። 16ዳዊት ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም፤ ወደ ክፍሉ ገብቶም ሌሊቱን መሬት ላይ ተኝቶ ዐደረ። 17የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያሰነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እምቢ አለ፤ አብሮአቸውም አንዳች ምግብ አልበላም። 18በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፥ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ። 19ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ አይቶ፥ ሕፃኑ መሞቱን ዐወቀ፤ ስለዚህ፥ “ሕፃኑ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “አዎን ሞቷል” ብለው መለሱለት። 20በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፥ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ጌታ ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ። 21አገልጋዮቹም፥ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት። 22እርሱም እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ ሕፃኑ በሕይወት እያለ፥ ‘ጌታ ይቅር ብሎኝ ሕፃኑን በሕይወት ያኖረው ይሆናል’ ብዬ ጾምሁ፤ አለቀስሁ። 23#ኢዮብ 7፥9-10።አሁን ግን ሕፃኑ ስለ ሞተ፥ የምጾመው ለምንድን ነው? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ፥ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም” አለ። 24ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። ጌታም ወደደው፤ 25ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ። 26#1ዜ.መ. 20፥1-3።በዚያን ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያንን ከተማ ራባትን ወግቶ የቤተ መንግሥቱን ምሽግ ያዘ። 27ከዚያም ኢዮአብ እንዲህ በማለት ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ “ራባን ወግቼ የውሃውንም ከተማ ይዤአለሁ፤ 28እንግዲህ የቀረውን ሠራዊት አሰባስበህ ከተማዪቱን ክበብና ያዛት፤ ያለበለዚያ እኔ ከተማዪቱን እይዛትና በስሜ መጠራቷ ነው።” 29ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ራባ በመሄድ ወግቶ ያዛት። 30የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱ ክብደት የሚመዝነው አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን፥ በከበረ ዕንቁም ያጌጠ ነበር፤ ይህም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ። ዳዊትም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤ 31እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፥ የብረት መቆፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ