1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 20
20
ዳዊትና ዮናታን
1 #
1ሳሙ. 19፥1-7፤11-17፤ 21፥11፤ 27፥4፤ ዘፍ. 31፥36። ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ካለችው የራማዋ ከናዮት ሸሽቶ ወደ ዮናታን በመሄድ፥ “ምን አድርጌአለሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገውስ በፊቱ ምን ተገኝቶብኝ ነው?” ሲል ጠየቀው። 2ዮናታንም፥ “ይህስ ካንተ ይራቅ! አትሞትም! እነሆ፤ አባቴ ትልቅም ይሁን ትንሽ ማናቸውንም ነገር አስቀድሞ ሳይነግረኝ አያደርገውም። ታዲያ አባቴ ይህንንስ ለምን ይደብቀኛል? እንዲህስ አይሆንም!” ብሎ መለሰለት። 3ዳዊት ግን፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው ጌታን! በነፍስህ እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ። 4ዮናታንም ዳዊትን፥ “እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር አደርግልሃለሁ” አለው። 5#ዘኍ. 10፥10፤ 28፥11-15፤ ዕዝ. 3፥5፤ ነህ. 10፥34።ስለዚህ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ነገ የወር መባቻ በዓል ስለሆነ፥ ከንጉሡ ጋር ምሳ መብላት ይጠበቅብኛል፤ ነገር ግን እስከ ከነገ ወዲያ ማታ ድረስ ከዱር ልደበቅ፤ 6#1ሳሙ. 17፥12።አባትህ ከፈለገኝ፥ ‘ለቤተ ዘመዶቹ ሁሉ ዓመታዊ መሥዋዕት የሚቀርብ ስለሆነ፥ ዳዊት ወደ መኖሪያ ከተማው ወደ ቤተልሔም ቶሎ ለመሄድ አጥብቆ ፈቃድ ጠየቀኝ’ ብለህ ንገረው። 7እርሱም ‘መልካም ነው’ ካለ፥ አገልጋይህን የሚያሰጋው የለም፤ ከተቆጣ ግን፥ ክፉ ነገር እንዳሰበብኝ ታረጋግጣለህ። 8#1ሳሙ. 18፥3፤ 23፥17-18።አንተ ግን ከአገልጋይህ ጋር በጌታ ፊት ቃል ኪዳን ገብታችኋልና ለአገልጋይህ በጎነትን አሳይ። እኔ በደለኛ ከሆንኩ፥ አንተው ራስህ ግደለኝ፤ ለምንስ ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ!” 9ዮናታንም፥ “ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ነገር እንዳሰበብህ ባውቅ ኖሮ እንዴት ሳልነግርህ እቀራለሁ?” አለው። 10ዳዊትም፥ “አባትህ ክፉ ቃል ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?” ብሎ ጠየቀው። 11ዮናታን፥ “ና! ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፤ ተያይዘውም ወጡ። 12ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ምስክር ይሁን! ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን፥ ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ፥ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤ 13#1ሳሙ. 10፥7፤ 17፥37፤ 18፥12፤ 14፤ 24፥22-23፤ 2ሳሙ. 9፥1-13፤ 21፥7።ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፥ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፥ ጌታ ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። ጌታ ከአባቴ ጋር እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋር ይሁን። 14እኔም እንዳልሞት፥ በሕይወት እስካለሁ የጌታን ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ 15ጌታ የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ ከምድረ ገጽ በሚደመስስበት ጊዜ እንኳ፥ ታማኝነትህ ከቤተሰቤ በፍጹም አይቋረጥ።” 16ስለዚህ ዮናታን፥ “የዳዊትን ጠላቶች ጌታ ይፋረዳቸው” በማለት ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። 17ዮናታን ከፍቅሩ የተነሣ ዳዊትን የሚወደውም እንደ ራሱ አድርጎ ነበርና ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ። 18ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ነገ የወር መባቻ በዓል ነው፤ መቀመጫህ ባዶ ስለሚሆን፥ አለመኖርህ ይታወቃል። 19#1ሳሙ. 19፥1-7።ከነገ ወዲያ ምሽት ላይ ይህ ችግር በተፈጠረ ዕለት ወደ ተደበቅህበት ስፍራ ሂድና ኤጼል በተባለው ድንጋይ አጠገብ ቆይ። 20እኔም በአንድ ዒላማ ላይ እንደሚያነጣጥር ሰው ወደ ድንጋዩ አጠገብ ሦስት ፍላጻ እወረውራለሁ፤ 21ከዚያም፥ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፥ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደሆነ፥ በሕያው ጌታ ስም! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ ውጣና ና፤ አደጋ እንደማይኖርም እምልልሃለሁ። 22ነገር ግን ልጁን፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት ከአንተ ወዲያ ዐልፎ ነው’ ያልሁት እንደሆነ ጌታ እንድትሄድ ፈቅዷልና ሂድ። 23አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ ጌታ በመካከላችን ለዘለዓለም ምስክር ነው።” 24ስለዚህም ዳዊት በዱር ተደበቀ፤ የወር መባቻ በዓል በተከበረበት ጊዜ፥ ንጉሡ ግብር ለመብላት ተቀመጠ፤ 25ንጉሡ እንደ ወትሮው በግድግዳው አጠገብ ተቀመጠ፤ ዮናታን ከፊት ለፊቱ፥ አበኔር ደግሞ ከአጠገቡ ተቀመጡ፤ የዳዊት መቀመጫ ግን ባዶ ነበር። 26#1ሳሙ. 16፥5፤ ዘሌ. 7፥20-21፤ 15፥1-3።ሳኦልም፥ “ዳዊት በሥርዓቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በእርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፥ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። 27በማግስቱም፥ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፥ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። 28ዮናታንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ዳዊት ወደ ቤተልሔም እንዲሄድ እፈቅድለት ዘንድ አጥብቆ ለመነኝ። 29እርሱም ‘ቤተሰባችን በከተማዪቱ ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያደርግ በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛልና ልሂድ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ወንድሞቼን ለማየት እንድሄድ አሰናብተኝ’ አለኝ። በንጉሡ ግብር ላይ ሳይገኝ የቀረውም በዚህ ምክንያት ነው።” 30ሳኦል በዮናታን ላይ እጅግ ተቆጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አንተ የዚያች ጠማማና ዐመፀኛ ሴት ልጅ! ለአንተው ለራስህ ውርደት፥ ለወላጅ እናትህም ዕፍረት ከሚሆነው ከእሴይ ልጅ ጋር መግጠምህን የማላውቅ መሰለህ? 31#2ሳሙ. 12፥5።የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንህ መንግሥትህ አትጸኑም። መሞት ስለሚገባው፥ ሰው ላክና አስመጣልኝ!” 32ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። 33#1ሳሙ. 18፥11።ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፥ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሣቱን ዐወቀ። 34ዮናታንም በታላቅ ቁጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። 35በማግስቱ ጠዋት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፥ ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ 36ልጁንም፥ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፥ ከእርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። 37ልጁም የዮናታን ፍላጻ ባረፈበት ስፍራ እንደ ደረሰ፤ ዮናታን ጠራውና፥ “ፍላጻው ካንተ ወዲያ ዐልፎ የለምን?” አለው። 38እርሱም “ቶሎ በል! ፍጠን! አትቁም!” ሲል ጮኸበት፤ ልጁም ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው ተመለሰ። 39ከዮናታንና ከዳዊት በስተቀር ልጁ ስለዚህ ነገር የሚያውቀው አንዳች አልነበረም። 40ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያውን ለልጁ ሰጥቶ፥ “ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። 41ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። 42#2ሳሙ. 9፥1፤ 21፥7።ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 20: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ