የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት መግቢያ

መግቢያ
ይህ የጴጥሮስ መልእክት የተጻፈው በመልእክቱ ውስጥ “የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ” በመባል ለሚጠሩትና በታናሽቱ እስያ ሰሜናዊ ክፍል ለተበተኑት ክርስቲያኖች ነው፤ የመልእክቱ ዋና ዓላማ በእምነታቸው ምክንያት ስደትና መከራ ደርሶባቸው የነበሩትን አንባቢዎች ለማበረታታትና ለማጽናናት ነው፤ ጸሐፊው ይህን የሚያደርገው የሞቱን፥ የትንሣኤውን፥ ተመልሶ የመምጣቱን ተስፋ የሚያበሥረውን የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች ቃል ለአንባቢዎቹ በማስታወስ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት በምሳሌነት በመመልከት መከራን በትዕግሥት መቀበል እንዳለባቸው ያሳስባቸዋል፤ ከዚህም ጋር በማያያዝ መከራ የእምነታቸውን ጥራት እንደሚፈትንና “ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ቀን” ተገቢ ዋጋቸውን እንደሚያስገኝላቸው ያስገነዝባቸዋል።
ጸሐፊው በመከራ እንዲታገሡ ከማደፋፈሩም ሌላ አንባቢዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች መኖር እንደሚገባቸው ዓይነት እንዲኖሩ ያሳስባቸዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-2)
የእግዚአብሔር አዳኝነት ማስታወሻ (1፥3-12)
የተቀደሰ ሕይወትን ለመኖር የተሰጠ ምክር (1፥13—2፥10)
በችግር ጊዜ የክርስቲያን ኀላፊነት (2፥11—4፥19)
የክርስቲያን ትሕትናና አገልግሎት (5፥1-11)
ማጠቃለያ (5፥12-14)
ምዕራፍ

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ